The Father of TPLF, Sebhat Nega

ከማተቤ መለሰ ተሰማ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ፡ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ እንደ ያኔው ናዚ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።

ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን በእቅድ ተነድፎ እየተከናወነ ያለ መሆኑን የህዋሀቱ አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ የአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝን የኢስሙላ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ሹመት አስመልክቶ ገዛ ተጋሩ ከተባለ ፓለቶክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፡ ስልጣንን ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታይና ከአማራ ነጥቀነዋል አላማችንም የኸው ነበር ሲሉ ሰነምግባር ባልገራው አንደበታቸው በድፍረት መናገራቸው የወያኔ ጉዞ ከየት ወዴትነት ማሳየት ከሚችሉ ኩነቶች እንደ አንዱ ሊወሰድ የሚገባው ነው።

ሟቹ ጠቅላይ አጥፊያችን አቶ መለስ ዜናዊም፡ በአንድ ወቅት ይህነን የበሰበሰ ሐይማኖት ኦርቶዶክስንና አማራን ካላጠፋን መሪት ትክበዳቸውና መቸም ስሟን መጥራት ያስጠላቸው ነበር፡ ሀአገሪቷን በምንፈልገው መንገድ መምራት አንችልም። ያሉ ሲሆን የህንኑ ቃል ሳይቀነስ እንዳለ ፡ አማራው የራሱ የሆኑ ልጆች አጥቶ በረከት ሰሞንን ከኤርትራ እንደተበደረ ሁሉ፡ ከደቡብ ኢተዮጵያ የተዋሳቸው አቶ ተፈራ ዋልዋ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲቫ በነበሩበት ወቅት ደግመውታል።

ለነገሩማ ህዋሃት በኢትዮጵያ አቆጣጥር 1968 ዓ.ም ደደቢት ውስጥ እያለ በነደፈው የትግል ማንፊስቶው ላይ፡ ከአላማው የመጀመሪያው አድርጎ ያሰፈረው አማራን ማጥፋት የሚል ነው። በዚህ መርሃ ግብሩ መሰረት ለ17 አመት ባካሄደው ጦርነት ሁሉ የሚማርካቸውን ወታደሮች ዘራቸውን በመጠየቅ አማራነኝ ያለውን ብቻ መርጦ እየገደለ ሌላውን ማለትም እንደ አባዱላ ገመዳና ኩማ ደመቅሳ አይነት ፈቃደኛ ምርኮኞችን ወደእራሱ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ ሲያደረግ አልፈልግም ያለውንና አማራ አለመሆኑ የተረጋገጠለትን ወደዬ ትውልድ መንደሩ ይመልስ ነበር።

ወያኔ በምዕራባውያን ሃአገሮች ሙሉድጋፍ የኢትዮጵያን መንግስትነት በትረ ስልጣን ከጨበጠ በሗላም የመጀመሪያ ስራው ያደረገው ሌላው ኢትዮጵያውያን በአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሕዝብ ላይ እንዲነሳ መቀስቀስ ነበርና፡ አቶ ታምራት ላይኔ በሃረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሴ፣ በቦረና። አቶ ዳዊይት ዮሀንስ ደግሞ በጀማ፣ በወለጋ በኢሉባቦር ወ.ዘ.ተ.ኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማህበረሰብ ባለበት ሁሉ እየተዘዋወሩ ይህ አማራ የተባለ ነፍጠኛ ለመቶ አመታት ሲዘርፍህ፣ ሲገፍህ ሲያሰቃይህ ኖሯል። አሁን ሜዳውም ፈረሱም እነሆ፡ ልትበቀለው ትችላለህ በማለት ቀስቀስው እንደተመለሱ በአርባጉጉ፡ በበደኖ፣ በባሌ፣ አርሴ፣ በቦረና፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፡ አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው እየተመረጠ፡ አነገቱ በሰይፍ እየተቆረጠ፣ እራሱ በፋስ እየተፈለጠ፣ ሆዱ በሳንጃ እየተዘነጠለ፣ ከእነ ህይወቱ በገደል እየጣለ በሸዎች የሚቆጠር ህዝብ ያለቀ ሲሆን፡ ወለጋ አሶሳ ውስጥ ደግሞ ከያለበት ተሰብስቦ በሳርቤት ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ በእሳት ተቃጥሏል። ይህ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አሁንም ተጠናክሮ ለመቀጠሉ፡ በቅርብ ከደቡብ ኢተዮጵያ ተመርጦ ንብረቱ እየተዘረፈ የተባረረው 75000 አማረኛ ተናጋሪ ምስክር ነው። ወያኔ እንዳቀነቀነውና ሌሎችም ተቀብለው እንዳስተጋቡለት፡ ነፍጠኝነት የብሔረስብ ወይንም የዘርና የሃይማኖት መገለጫ አለዚያም የመደብ ባህሪ መከሰቻ አይደለም፡ ታሪክን አጣምሞ በመተርጎም እርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በማለም እንጅ። ነፍጠኛ የሚለው ስም በአንድ ወቅት በሔረሰብ ሳይመርጡ ጎሳ ሳይለዩ ኢትዮጵያውያን፡ ለሃገር አንድነትና ነጻነት ተዋግተው እንዲሞቱ፡ ግዳጅ ሲሰጣቸው የተዋጊነት መለያ የተሰየመላቸው ስም ነበር እንደዛሪው ወታደር። በዚህ ግዳጅ ደግሞ የተሳተፈው አማራው ብቻም አልነበረም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንጅ፡ ዛሪ በምን መለኪያ ተመዝኖ ለአማራው እንደተሰጠና እንዴትም ስድብ እንደሆነ አይገባኝም።

የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ የተገፋው በሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊና አካባቢ በቻ አይደለም፡ ክልልህ ነው በተባለውም በከፋ ሁኔታ የቀጠለ ነው እንጅ። አማራው የሚያስተዳድረው የሚመራው ከራሱ አብራክ ያወጣው በሙያው የተካነ ልጅ እንደሌለው ተቆጥሮ የአማራ ክልል መሪ ሆነው ለረጅም አመት የተቀመጡት ከትግራይ ክልል ሄደው ምዕራብ ሃረርጌ፡ ሀብሮ አውራጃ ሂረና ወረዳ ከሰፈሩት ከቄስ ለገሰ የተወለዱትና የ1ኛ ደረጃ ት/ ቤት የእስፖርት አስተማሪ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ሲሆኑ እኝህ ባለስልጣን የስራ መጀመሬያቸው ያደረጉት ህዝቡ እንዲሸማቀቅ፣ በማንነቱ እንዲያፍርና አንገቱን እንዲደፋ ሞራሉ፣ ምግባራዊ ድፍረቱና ሰባዊመብቱ ከውስጡ እንደጭስ እየተነነ እንዲጠፋ ለማድረግ፡ በአንድ ወይንም በሌላ መንገድ ከማህበረሰቡ የተገለሉ፣ ታሪካቸውን ለጥቅማቸው፣ ሰብናቸውን ለሆዳችው አሳልፈው የሸጡ ደካሞችን በመመልመል በዘለፋና በስድብ አሰልጥነው በማሰማራት በጀምላ ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ጥገኛ፣ ቢሮክራት ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ውርጀብኞችን በስፋት ማሰራጨትን ነበር።

ከዚያ በመቀጠል በመጀመሪያ ከሌሎች ክልሎች በተለየ በአማራ ክልል ከረጅም አመታት ጀምሮ የነበረውን የወባ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጠቅላላ በመዝጋት ከ1984 እስከ 1987 ድረስ የወባ ወረርሸኝ ገብቶ ከአንድ ቀበሌ በቀን ከ10 እስከ 15 የሚደርስ ሰው እየሞተ ቀባሪ እንኳን ያጣበት ሁኔታ ሲከሰት እንደ መንግስት አንድም የመከላከል ሙከራ ካለመደረጉም በላይ፡ በጤና ተዋልዶ ፕሮግራም ሰበብ አሁንም በየትኛውም አካባቢ ያልተሞከረውን፡ አርሶ አደሩን በገንዘብ በማባበል፣ እንቢሲል በማስፈራራትና በማስገደድ ወደፊት ዘር እንዳይተካ የዘር ብልቱን በሀኪሞች እንዲነኮላሽ በማድረግ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን በከፍተኛ ደረጃ አካሂደውበታል፡ ዛሪም ይህ እኩይ ድርጊት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሌላ በኩል ነግዶ አደሩን በዝባዥ፣ ጥገኛ ባለሀብት በማለት። እንደ ዶሮ ከጉልበቱ በላይ ለብሶ ያለመጫሚያ የሚኳትነውን አርሶአደር ደግሞ ቢሮክራት፣ ንክኪ በማለት፡ ንብረትና መሪቱን በመንጠቅ፡ ቅዬውን እየለቀቀ እንዲሰደድ፡ በማድረጋቸው 1993 ዓ.ም ህግና መንግስት ያለ መስሎት፡ አዲስ አበባ ድረስ ተጉዞ ፒያሳ ከሚገኜው ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመስፈር፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር እየተፈራረቀበት እራብና ጥም እያሰቃየው ፍትህ ቢለምንና ቢማጸን ከወያኔ መንግስት ያገኘው መልስ ድብደባ እስራትና ግድያ ነበር፡ በዚህ ወቅት ከ80 የማያንሱ ሰዎች ለአቤቱታ እንደወጡ በወያኔ ደህንነቶች ታፈነው የት እንደደረሱ እስካሁን አይታወቅም። የተረፈው ሕይወቱን ለማሰንበት ሲል ወደወለጋ በመሄድ ጦማደር መሪት መርጦ ስፍሮ መኖር ሲጀምር፡ ደገሞ የወያኔ ካድሪዎች ወራሪ ጠላት የመጣበት በማስመሰል የአካባቢ ኗሪ የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነውን ማህበረሰብ ቀስቅሰው በማስነሳት ከአማራ ክልል ሄዶ በሰፈረው ህዝብ ላይ ጦርነት አስከፍተው፡ ሴትና ሕጻናትን እንኳን ሳይተው በጅምላ  በመጨፍጨፍ ከ6000 ያላነሰ   አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ እንዲያልቅ አድርገዎል።

ከዚህ ተርፎ ምንም ንብረት ሳያንጠለጥል፡ ሚስት የባሏን ባል የሚስቱን ወላጅ የልጁን ልጅ የወላጁን እሪሳ እየተራመደ አባይን ተሻግሮ ጎጃም ቡሪ ከተማ ሲሰፍር የማስተናገድ ሃላፊነት የነበረባቸው የአማራ ክልል ባለስልጣናት፡ ዞር ብለው አለማያት ብቻ ሳይሆን ግብርሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡት እርዳታ ፈጥኖ እንዳይደርስ ቢሮክራሴያዌ መሰናክል በመፍጠር በርካታ መዳን የሚችሉ ቁስለኞች እንዲሞቱ አድርገዋል። በእነዚህና የመሳሰሉ የረቀቁ የዘር ማጥፋት ዘዴዎች ያለቀውን አማረኛ ተናጋሪ በተመለከተ ከሁለት አመት ገደማ በፊት በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ሪፖርት 2.4 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ እንደተወገደ ለፓርላማው በኩራት ተገልጿል። በተዘዋዋሪ የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻችን በእቅዱ መሰረት ግቡን እየመታ ነው የሚል ሪፖርት እንደሆነ ነው ለእኔ የሚሰማኝ።

እንዲህ ገፋገፋ እስከዳር ነው እንጅ፡

መሀል መሃል ስንል አስወጡን ከደጅ።

እንዳሉት አቶ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አማረኛ ተናጋሪው ህዝብ፡ በወያኔም ሆነ በሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኑ እንዲህ እስከመጨረሻው ዳር ድረስ ሊገፋ የቻለበት ምክናያት ምንድን ነው? እንደዚህ በእየቦታው የሚሳደደው፣ የሚገደለው፣ የሚዘረፈው፣ የሚገፈፈው፣ የሚዋረደው ለምንድን ነው? ምን ስለአጠፋ ነው? አስቀድሞ የተሰራ በደል ካለስ? ያሁኑ ትውልድ የቅድመ አያቱን እዳ መክፈል አለበት ወይ? ደግሞስ የትኛው መሪ ነበር አማራና ዛሪ አማራ እንደተጠያቂ የሚታይው? ምኒልክ እናታቸው ኦሮሞ ነበሩ፣ ሀይለ ስላሴ እናታቸው ጉራጌ ሲሆኑ አባታቸው የኦሮሞው ተወላጅ መኮንን ጉዴሳ ናቸው ፣ መንግስቱ አባታቸው ኦሮሞ ናቸው። ምን ስለሆነ ነው ተጠያቂ የሚሆነው? አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማህበረሰብስ፡ ከየአቅጣጫው ይህ ሁሉ ማት ሲወርድበት፡ ለምንድን ነው ዝም ብሎ የተቀመጠው? በእውነት ወያኔ እንደሚለው ፈሪና ሽንታም ስለሆነ ነው? በእውነት አማራ እራሱን መከላከልና ቃታመሳብ የማይቸል ደካማ ፍጡር ነው? ወ.ዘ.ተ.የሚሉ ጥያቄዎች ዘወትር እንደ ስራት አልባ የጉንዳን ሰራዊት በአእምሮዬ እንደተተራመሱ መልስ ሳያገኙ፡ ቀንን ቀን እየተካው የማያቋርጠው የወራት ጎርፍ እያጋፈለ አልፎ ጊዜ በነበር ጢሻውስጥ በመስረግ ላይ ነው ያለው።

አሁንም ከአቶ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ግጥም አንድ ስንኝ ልዋስ

አትንኩኝ ባይ ነበር እስከ ትናንትና

እረ እግዚወ በሉ ወዴት ሄደ ጀግና

እንዳሉት እኔን እንደሚገባኝና በታሪክ እንደማውቀውም አማረኛ ተናጋሪው፡ ኢትዮጵያዊ ትናንት ከእራሱ አልፎ ሀገር ሲወረር ድንበር ሲደፈር፡ ቀድሞ ደርሶ ከአእምሮ፣ ከጉልበት፣ ከጊዜና ከገንዘብ ባሻገር የአካልና የህይወት መሷእትነት ሲከፍል የኖረ ነበር፡ ዛሪ ግን ቀኝህን ሲመታህ ግራህን አቅርብለት እንደሚለው ስብከተ ሃይማኖት አይነት አቋም በማራመዱ ተፈርቶ ሳይሆን ተንቆ ከመጠላትና እራሱን መከላከል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሷል። ለምን? ይህነን ጥያቄ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሊመልሰው የሚገባ ነው ብዬ አስባለሁ፡

ጥንት አባቶቻችን አነበሶች ነበሩ

እኛስ ደመት ሆነ ምንድን ነው ነገሩ

  እንደተባለው ከእያቅጣጫው እንደዚህ ሲገፋና ይህ ሁሉ የግፍ አዝመራ ሲወቃበት ዝም ብሎ እንዲቀበል ያደረገውን ነገር አንጥሮ በማወቅ ሌላው ቢቀር ዘርን ከመጥፋት ለመከላከል እንኳን ለምን ማለትን መጀመር የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተገዶ የሚገባበት ሃቅ ይመስለኛል።

የከፋው ሲያለቅስ ደስ ያለው ሲዘፍን

ያለው ሞልቶት ሲያፈስ የሌለው ሲለምን

እንዳሉት አዲስ ዓለማየሁ ወያኔዎች ሲዘፍኑ ሞለቷቸው የውጭ ሃገር ባንክን በገንዘብ ሲያጨናንቁ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማህበረሰብ ግን ለ21 አመት በርሀብ፣ በእርዛት፣ በሰው ሰራሽ በሽታ፣ በዱላ፣ በጎራዴ፣ በሳንጃ፣ በጥይት በገደል፣ በእሳት ወ.ዘ.ተ እንደቅጠል እረግፏል፡ የተረፈውና ነገ ምን ይደርስብኝ ይሆን በማለት ስጋው በስጋት አልቆ ያለምንም በህይወት የመቆየት ዋስትና ፡ቀጣይ መጻቱን በመጠባበቅ ላይ ያለውም ቢሆን ዛሪ ዘርቶ መቃሚያ፣ ወልዶ መሳሚያ፣ ፈትም መኖሪያ በሗላም መቀበሪያ ሃገር ተነፍጎና እስከመጨረሻው ተገፍቶ በገዛ ሀገሩ ላይ ስደተኛ ሆኖ ነው ያለው። እንግዴህ ከዚህ የከፋ ምን እስኪመጣ ይሆን የሚጠበቀው???? ይሁዲዎች ልክ እንደ አሁኑ አማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ህዝብ በሁሉም ሲገፉ፡ እራሽያና ኢትዮጵያ ከለላ ሰጥተዋቸው ነበር። አማራውን ግን በወደቀ እንጨት ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ፡ ቤተክርስቲያን ወይንም መስጅድ እንደገባች ውሻ የሁሉም ክንድ መሞከሪያና አፍ መፍቻ ነው የሆነው፡፡ ይሁዲዎች ዘራቸው ሳይጠፋ ለዛሪው ደረጃ የደረሱት በዝምታ ሳይሆን እራሳቸውን በመከላከላቸው ነው። አማራውስ?????

ሃገሩን አልከዳ ወገን አልበደል፡

ምነ እንዲህ ተገፋ ኢትዮጵያን ባለ፡

እንዲህ ተነገረ በድፍረት ተወራ፡

ሽንታም ነህ ተባለ ዝም ሲል አማራ፡

አዎ! ሽንታም ነበር እጅግ ዘረ ብዙ፡

ድንበር አስከባሪ በደሙ በወዙ፡

እርግጥ አማረኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ፡ ማንነቱ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። የዘር፣ የሃይማኖት የቋንቋ ልዩነትንም አያውቅም። አማረኛ ተናጋሪውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ደምና ስጋ ናቸው። አንዱ ካለ አንዱ የማይኖሩ። ወያኔ በድርጊት ፕሮግራም ነድፎ ለ21 አመት የሰራበትም፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በመጅመሪያ አማረኛ ተናጋሪውነና የኦርቶዶክስ እምነትን ማጥፋትን ነው።

እነመለስ፣ ሰብሀትና ተፈራም ሲነግሩን የኖሩትና እየነገሩን ያሉት ይኸንኑ ሃቅ ነው። አሁን ያለው አማራጭ ሁለት ነው እሱም ወያኔ እቅዱን ይፈጽም ዘንድ እጅን አጣጥፎ በመቀመጥ ዘርም ሃይማኖትም፣ ሃገርም ሲጠፉ ማያት፡ ወይንም እንቢ ብሎ ሁሉንም ከጥፋት ማዳን ነው። እራስን፣ ሃይማኖትንና ሃገርን ከጥፋት ለመከላከል ደግሞ የግድ በቋንቋና በሃይማኖት መደራጀትን የሚጠይቅ አይደለም። በእያለበት ድርጅትም ሆነ የስራ መስክ እራሱን ለማስከበር ቆራጥ እርምጃ መውሰድና ለሚሰነዘርበት ተንኮሳ ሁሉ ነገሮችን ሳይንቅ ፈርጣማ አጻፋውን ከምርና በቁጭት መመለስ ከቻለ በቂ ነው።

እስካሁን አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ በመለሳለሱ በሁሉም ወገኑ በሁሉም አቅጣጫ እስከመጨረሻው ጠርዝ ድረስ ተገፋ፡ ስደት፣ ውርደት፣ ሞት ተፈረደበት፡ ሽንታም ነህም ተባለ፡ አጥንት የሚሰብር ውርደት ደረሰበት፡ በሀገሩላይ ስደተኛ ሆነ፡ በየሄደበት ተናቀ ተደቀደቀም፡ አይበቃም ወይ፡????

ኢሜል matebemelese@yahoo.com

1 COMMENT

  1. Dear Matebe Melesse
    Your writing is so poor, not b/c of idea (you have all rights to convey what ever it is). Instead, b/c of language. Are you really from Amhara? I doubt b/c you could not have made several mistakes between “saliis” and “sadiis” which an ordinary Amhara person knows, had you been really a real HABESHA. I can see that this writing is from some one who dislikes Amhara.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here