በታላቁ አንዋር መስጂድ የተከሰተው ፍንዳታ የአካል ጉዳት አስከተለ

0

በታላቁ አንዋር መስጂድ  ከጁምኣ ሰላት በኃላ በደረሰ ፍንዳታ በመስጊዱ ቅጥር ግቢ የነበሩ ሙስሊሞች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው የታወቀ ሲሆን
ፍንዳታው የደረሰው  ከጁምአ ሰላት በኋላ በቅጥር ግቢ ውስጥ የመውሊድን በአል በማስበልከት የተስባስቡ ምእመናን ላይ ነበር ፡፡
አርብ ህዳር 1 2008 አደጋው ከደረሰ በኋላ በመስጂዱ የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት  በፍጥነት የደረሱ ሲሆን መስጂዱም እስከ አስር ሰላት ወቅት ድረስ ተዘግቶ እንደነበር ተገልፆል፡፡
አደጋው በተፈጠረ በቅፅበት ፖሊሶች በመስጂዱ ውስጥ ሊደርሱ የቻሉበት ምክንያት ግርምትን የፈጠረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማንኛውም ሚዲያ ወይም ግለሰብ ቀረፃ እንዳያካሄድ የመስጂዱ አስተዳደርና ካዲሞች ሲከለክሉ እንደበር ታወቆዋል  የኢቲቪ ጋዜጠኞች ግን በቦታው በመገኘት በነፃነት ቪዲዬ ቀርፁው እና ፎቶ አንስተው ሄደዋል በአስር ሰላት ወቅትም መስጂዱ ተከፍቶ ሙስሊሙ ገብቶ ሰላቱን የሰገደ ሲሆን በመስጂዱ ያለው ሁኔታ አስር ሰላት ላይ መረጋጋቱ ተገልፆል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናን በተክለሃይማኖት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
የመንግስት ሚዲያ የሆነ ፋና ብሮድካስቲግም በአንዋር መስጂድ አካባቢ ቦንብ ፈንድቶ የተወሰኑ ሰዎች ላይ አደጋ ማድረሱን የመንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ሚኒስተር የሆነውን አቶ ጌታቸው ረዳን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY