አባይ ሚዲያ
ሱራፌል አስራት

የአዲስ አበባ የልብ ሕሙማኖች ሆስፒታል (Addis Cardiac Hospital) መስራች እና ስራ አስክያጅ የነበሩት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በተከሰሱበት የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ናቸው ተባሉ። ዶ/ር ፍቅሩ የቀድሞው የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣንና በአሁኑ ግዜ በስር ላይ ከሚገኙት ከነአቶ መላኩ ፈንታ ጋር በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወቃል። በዚህ ወንጀ ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙ ተጠርጣሪወች መካከል ዶ/ር ፍቅሩ የመጀመሪያው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተወስኖባቸዋል።
የስዊድን ዜግነት ያላቸው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የአራት አመት ከስድስት ወር እስራት እና የሶስት ሺ ዶላር የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። ዶ/ር ፍቅሩ ከታሰሩ ከሶስት አመት በላይ እንደሆናቸው ቢታወቅም በአመክሮ ይፈቱ ወይንም አይፈቱ እስከአሁን የታውቀ ነገር የለም።