አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመፅ አዲስ አበባን ጨምሮ በተቀሩትም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሔደ ያለዉ አመፅ በዉይይቱ ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንድሚፈጥር ካይሮ የሚታተመው ካይሮ ፐልስ ዘግቧል። የሕዳሴ ግድቡን በተመለከተ የሕዉሓቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደብረፅዮን ሥራዉ 54 ከመቶዉ መጠናቀቁን በመግለፅ አሁንም የግድቡ ሥራ እየተቀላጠፈ መሆኑንም አያይዞ በኦክቶበር 17 መግለፁ ይታወቃል።

በኦሮምያ ማሕበረሰብ በተነሳዉ ሕዝባዊ አመፅ መነሻ የሆነዉ የሕዉሐት አስተዳደር የገበሬዉን መሬት ያለ ፍላጎታቸዉ ባልተመጣጠነ ዋጋ ከገበሬዉ ላይ እየገዛ አሊያም እያሰገደደ ለዉጭ ባለ ሃብቶች መሸጡን ምክንያት በመሆኑና የአካባቢዉም ገበሬ ለሥራ አጥነት በመዳረጉ ቤተሰቡንም ማስተዳደር ባለመቻሉና ከዚህም ጋር ተያይዞ የአንድ ዘር የበላይነት በችግሩ ላይ ተጨምሮ ከፍተኛ ሁከት በሁሉ የአገሪቷ ክፍል መነሳቱ ከዚህም ጋር ተያይዞ የዘረኛዉ የሕዉሐት አገዛዝ በወሰደዉ እርምጃ ከ500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዉያኖች መገደላቸዉ ችግሩን ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል።

የአዲስ አበባዉ የሕዉሐት አገዛዝ በዉጭ ጉዳዩ ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ አማካኝነት የካይሮን መንግስት አሁን ላለዉ በኢትዮጵያ የሚካሔደዉን አመፅ በተለይም በኦሮሞ ማሕበረሰብ እየተካሔድ ያለዉን ሕዝባዊ አመፅ አስመልክቶ አዲስ አበባ ላለዉ የግብጽ ኢምባሲ ለአምባሳደር አቡበከር ኤፍኒ ይህንን አመፅ ከኋላ ሆናችሁ ምትረዱት እናንተ ናችሁ በሚል ለዉይይት መጥራታቸውን አስታዉሶ የካይሮ መንግስትም በዕለቱ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል ለቀረበበት አቤቱታ ምላሹን ባወጣዉ መግለጫ አፀፋዉን ሰጥቷል።

አምባሳደሩም መግለጫዉን አስመልክተዉ በሰጡት ቃል አንዳንድ ፓርቲዎች በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ጣልቃ መግባት የሚፈልጉ አሉ ነገር ግን ግብፅ በኢትዮጵያ ዉስጥ መረጋጋት እንዲኖር የሁል ጊዜም ፍላጎቷ ነው ብለዋል።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኦክቶበር 12 በሰጠዉ መግለጫ በሕዉሐት በኩል የቀረበበትን ክስ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት የዜና አዉታሮች ግብፅ ተቃዋሚዮቼን በሥልጠና በገንዘብ ዕና በትጥቅ ትረዳለች የሚለዉን ክስ አጣጥለዉታል። የሕዉሐት የግኑኝነት ሚኒስትሩ ጌታቸዉ ረዳ እንዳለዉ ኤርትራና ግብፅ በቀጥታ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱትን በገንዘብ በሥልጠና ዕና በትጥቅ እንደሚረዱ ገልጾ ምን አልባትም እነዚህን ተቃዋሚዎች የሚረዳዉ ክፍል በቀጥታ የግብጽ መንግስት ዕጅ አለበት ባይባልም ነገር ግን ግብፅ ዉስጥ ባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኩል የመሳሪያ አጠቃቀም እርዳታዉን ሊያገኙ እንደሚችሉ በመግለጽ በቀጥታ ይኼ መንግስት ያ መንግስት ብለን መንግስታቶችንን ባንጠቁምም በርካታ የሆኑ ቀጥታ ግኑኝነት ያላቸዉ አካሎች እንዳሉ አያይዞ ገልጿል።

በጦር ሃይሉ ዋና ፅሕፈት ቤት በነበረዉ የትምህርት ሴሚናር ላይ ፕሬዚደንት አብደል ፈታ አልሲሲ ባደረጉት ንግግር ግብጽ የኢትዮጵያዉያንን ተቃዋሚዎች በመርዳት በኢትዮጵያ ላይ ችግር መፍጠር እንደማትፍልግ እና ሊሆን የሚችል ጉዳይ እንዳልሆነም ሲገልፁ ምንም እንኳን ግብፅ ችግሩን ለመቋቋም አቅም ያላት ቢሆንም ከመንግስቱም ጋር በትብብር ለመሥራት እንደሚፈልጉም ገልፀዋል።

ኖሐ ባካር የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ፕሮፌሰር እና በካይሮ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ መምሕር የሆኑት የሕውሐትን ክስ አስመልክተዉ በሰጡት አስተያየት ከዚህ ክስ ጋር ተያይዞ አብሮ መታየት ያለበት ብለዉ መንግስታቸዉን ያሳሰቡት ኢትዮጵያ ግብጽን ለማሳሳት የተጠቀመችበት ነዉ ብለዋል። የክሱም አላማ በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉትን ስምምነቶች መስመር ለማሳት ነዉ በማለት ተችተዋል።

ባለፈዉ ሴፕቴምበር 20 በግብጽ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል የመጨረሻዉን ስምምነት በቴክኒካል ልዑካኖቻቸዉ አማካኝነት በየትኛዉ ካምፓኒ ጥናቱ እንደሚጠና ስምምነት ላይ ደርሰዉ መፈራረማቸዉን አስታዉሶ የዉሐና ፍሳሽ አገልግሎት መስሪያ ቤትም ታሪካዊ አጋጣሚም ነዉ ብሎ በመግለጽ የግድቡ ግንባታ በግብጽ ላይ በእርሻ በኢንዱስትሪና በመጠጥ ዉሃ ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ገልፀዋል።

በከር በጋዜጣዊ መግለጫቸዉም ላይ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የምታደርገዉን ስምምነት (Declaration of Principles and the Khartoum Agreement) የስምምነቱ ሰነድና የካርቱም ዉልን ጨምሮ መቋጨት ላይ መድረስ እንዳለባት ሲገልፁ አያይዘዉም ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የዉስጥ ችግር ምክንያት በማድረግ ስምምነቱ እንዲጓተት እያደረገች እንደሆነም ገልፀዋል።

በ ዲሴምበር 15 በሶስቱም መንግስታት የካርቱሙን ስምምነት የተፈራረሙት በ ማርች 2015 የየአገራቱ ፕሬዚደንቶች Declaration of Principle በተፈራረሙበት ሰነድ መሰረት በማድረግ ነዉ።የዚህ ሰነድም በግድቡ አጠቃቀምና የዉሃ ፍሰቱን በተመለከት የ 3ሰቱም አገራትን ትብብር የሚመለከት ነዉ።

በተባበሩት መንግስታት የግድብ ንድፍ እና ዉሃ ኤክስፐርት የሆኑት አሕመድ  ሸናዊ እንዳሉት የኢትዮጵያ ባለ ስልጣናት ግድቡን አስመልክቶ የሚሰጡት መረጃዎች እርስ በራሱ የሚቃረን ነው በማለት የመስኖ ሚኒስተሩ እና ካይሮ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር የግድቡ ዉሃ ማቆሪያ 190 ሜትር ነዉ ሲሉ አዲስ አበባ ያሉት ባለ ስልጣኖች ደሞ 145 ሜትር ነው የሚል መረጃዎችን መስጠታቸዉ በማስረጃነት ይገልፃሉ።

ሼናዊ የግብጽ ዉሃ ሃብትና የመስኖ ሚኒስትር መስሪያ ቤት የዉሳኔ ሃሳብ መስጠት አለመቻሉምንም ወረፍ አርገው ይኼን ማድረግ አለመቻላቸዉ ደሞ በሥራዉ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ለአልሞኒተር ጠቁመዉ አልፈዋል። በማያያዝም የናይል ተፋሰስ ባለቤት የሆኑት አገራት ግብጽን ዉሃ በኪዩቢክ ሜትር ለማስከፈል ዉይይት እያደረጉ መሆናቸዉንም በመግለጽ በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ጥናቱን በሚያካሒዱት ካምፓኒዎች በሚወጣዉ ዉጤት መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ ችግሩ እየተባባሰ ሊሔድ ስለሚችል አለም አቀፍ አማካሪዎች በጉዳዩ ጣለቃ መግባት እና መፍትሔ መስጠት እንዳለባቸዉም ያ ካልሆነ ግን ግብጽ ልታስገድድ የምትችልበት መብት እንደሌላትም አያይዘዉ ገልፀዋል።

የቀድሞው የመስኖና የኃይል ሚኒስትር የነበሩት አለማየሁ ተገኙ ለሱዳን ትሪቡን ባለፈው አመት በሰጡት ቃል በወቅቱ የነበረዉን ዉይይት በሶስቱ አገሮች መካከል ስለሚኖረዉ ስምምነት እንጂ ግድቡ ምን ያህል ዉሐ ይይዛል የሚል እንዳልነበረ እና በዛን ጊዜ ኢትዮጵያ በምንም ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ስምምነት ላይ እንዳልደረሰች ገልፀዋል።