Ethiopia Soldiers in trucks (from file)

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የእንቢተኝነት ፍልሚያ ታላቅ ስጋት ውስጥ የከተተው ወያኔ ስጋት የሌለባቸው ከሚላቸው ቦታዎች የሚገኙ ወታደሮችን ወደ ስጋት ቀጠናው እያጓጓዘ መሆኑ ታወቀ፡፡ ተጨማሪ ክ/ጦሮችንም እየመሰረተም መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተለይም በጎነንደር የተለያዩ ስፍራዎች እየተጠናከረ የመጣውን የአርበኝነት ትግል መቋቋም እየተሳነው የሄደው የወያኔ ጦር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተለይ ስጋት የሌላቸው ካላቸው ከትግራይ ክልል መቀሌና አድዋ የመሳሰሉ ቦታዎች የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ጎንደር እያጓጓዘ መሆኑን የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የስጋት ቀጠና ወደ ተባሉት የጎንደር አካባቢዎች ተጨማሪ ሰራዊት እንዲሰፍር ከማድረግ በተጨማሪ አዳዲስ ክ/ጦሮችን እየመሰረተ መሆኑንም ጨምሮ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ከተመሰረቱት ክ/ጦሮች ውስጥም 46ኛ ክ/ጦር ጎንደር ላይና 17ኛ ክ/ጦር ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መመስረታቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here