አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

በኢትዮጵያ ያለዉን ሕዝባዊ አመፅ ተከትሎ የቱሪዝም ገቢ በሚያስደነግጥ አይነት ማሽቆልቆሉ ፋይናንሺያል ታይምስን ጨምሮ መዘገቡ ታወቀ።

ይህንን ሕዝባዊ አመፅን መቀጣጠል ምክንያት በማድረግ አሜሪካ፤ አየርላንድ፤አዉስትራሊያ፤እንግሊዝ፤ እንዲሁም ካናዳን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያለዉን አለመረጋጋት አሳሳቢ በመሆኑ ዜጎቻቸዉን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ መክረዋል።

በአዲስ አበባ የመሬት ማስተር ፕላን ተመልክቶ የተቆሰቆሰዉ የሕዝብ ቁጣ ከ500 በላይ የሰዉ ሕይወት የቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩትን በወያኔ የማሰቃያ ዕስር ቤት ዉስጥ መታጎራቸዉ የሚታወስ ሲሆን የኽዉ አመፅ በአዲስ አካባቢ ዙሪያ በነበረዉ ሕዝባዊ አመፅ የአንዲት አሜሪካዊት ሕይወትን መቅጠፉም የሚዘነጋ አይደለም።

አንዳንድ የቱሪዝም ካምፓኒዎች ጥንታዊት አገርን እና ዉብ የተፈጥሮ ሃብት የታደለችዉን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በየካምፓኒያቸዉ የተመዘገቡትን ደንበኞቻቸዉን አሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ወደ አካባቢዉ መሔዱን እንደማይመክሩ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከፍተኛ ገቢ ከምታገኝባቸዉ ተቋማት አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከበርካታ አገሮች በርካታ ቱሪስቶች ላለፉት 10 ዓመታት አገሪቷን እንደጎበኙ ይታወቃል።