ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጠባቂን(HRW) ሁከት በማነሳሳት ከሰሰች።

የወያኔ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጠባቂን( Human Right Watch) ስለ ኢትዮጵያ የተሳሳተ ዜና በመስጠት ተቃዋሚዎች ሁከት እንዲፈጥሩ ያበረታታሉ ሲል ከሰሰ።

የሰዎች መብት ጠባቂ ቡድን( Human Right Watch) በቅርቡ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰውን የመብት ጥሰት አስመልክቶ ያቀረበውን ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ  አድሃኖም የበለጠ ሁከት ለመፍጠር ታስቦ የተደረገ መሰረት የሌለው እና የፈጠራ መግለጫ ነው ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሰብዓዊ መብት ጠባቂው ለቀረበው ሪፖርት   ፌሊክስ ሆርንን (Felix Horne, Senior Researcher ) የተሳሳተና አሉታዊ ዘገባ በማቅረብ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን ተቃውሞ ያነቃቃ ነበር በማለት ወንጅሎታል። በዚህም ሳያበቃ ከኢትዮጵያ መንግስት ሚዲያ ምንም አይነት ኢንፎርሜሽን ሳይጠይቅ ስለነበረው ተቃውሞ ፅሁፍ ማውጣታቱን፤በኢሮፕ ፓርሊያመንት ንኡስ ኮሚቴ( Europian Parliament sub Committee) ጉዳዩን ማቅረቡን ሲአቀርብም የኢሮፕ ፓርሊያመንት በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን የመብት ጥሰት በገለልተኛ ክፍል ምርመራው እንዲካሄድ ግፊት እንዲአደርጉ ለማሳመን የተጋነነ እና የፈጠራ ሪፖርት አቅርቧል ሲሉ የክስ ውርጅብኝ በማውረድ የቀረበውን ሪፖርት አጣጥለውታል።

ምንጭ Sudan Tribune