የኦሮሞና አማራ ህዝቦች ታሪካዊ  ባላንጣነት ማስወገጃ መንገዶች 

 

 1. በሁለቱ ህዝቦች መካከል የመተባበርና መቀራረብ የሚያሳዩ መፈከሮችን በተለያዩ ሠላማዊ ሰልፎች የህዝብ መገናኛ ቦታዎች የፓረቲዎች ስብሰባዎች እና ቃለመጠይቆችን ማድረግ
 2. የአማራ ልጆች ኦሮሞኛ እንዲማሩና የኦሮሞ ልጆች አማርኛ አንዲማሩ ማስቻል
 3. መልካም የታሪክ ትስስሮችንና አጋጣሚዎችን በማጉላት ማስተማር
 4. መጥፎ የታሪክ ትስስሮችንና አጋጣሚዎችን በመቀነስ ከታሪክ ማስወገድ
 5. የባላንጣነት ሐውልቱን ማፍረስና ማስወገድ
 6. አማራዎች በኦሮሚያ ክልልና ኦሮሞዎች በአማራ ክልል በማስፈር ህዝባዊ ትስስር መፍጠር
 7. አማርኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎችን በአማራ ክልል አመራር አድርጎ መሾም እና ኦሮሞኛ ተናጋሪ አማራዎችን በኦሮሚያ ክልል አመራር አድርጎ መሾም
 8. ማንኛውም ዜጋ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል መስራትና መሾም እንዲችል ማመቻቸት
 9. የአሁኑ ሥርዓት በሁለቱ ብሄሮች መቃቃር ላይ የሰራው ሴራ በሰፊው ለህዝቡ ማሳወቅና ማጋለጥ
 10. የሚመሰረተው መንግስት ላይ ከሁለቱ ብሄሮች በብዛት ከተውጣጡ ምሁራንን በመመልመል አመራር አድርጎ መሾም
 11. የሁለቱ ብሄሮች ቋንቋዎች የሀገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋዎች አድርጎ መወሰን
 12. በሁለቱ ብሄሮች መካከል የሚደረጉ የጋብቻ ትስስሮችን ማበረታታት
 13. ሁለቱ ብሄሮችን የሚያጣምሩ ሙዚቃዎች ትያትሮች ፊልማች ድራማዎች ግጥሞች መስራት
 14. ብሄር ለብሄር የሚጣምሩ እስፖርታዊ ውድድሮችን ማካሄድ
 15. የኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችና አባቶች በአማራ ክልል የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችንና ፈብሪካዎችን አንዲጎበኙ ማመቻቸትና የአማራም ወጣት ተማሪዎችና አባቶች በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችንና ፈብሪካዎችን አንዲጎበኙ እንደዛው ማመቻቸት
 16. ከሁለቱ ብሄሮች ያሉ አባቶች በኢቲቪ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ታሪካዊ የዕርቅ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ማድረግ
 17. የሐይማኖት አባቶችና ተቋማት የዘር ለዘር ማቀራረብ ሥራ እንዲሰሩ ማድረግ
 18. የዩኒቨርስቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከራሳቸው ክልል ውጪ መመደብ
 19. በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ክበቦቸ የብሄር ለብሄር እንዲቀራረቡ ማድረግ
 20. የአማራ ልማት ማህበር ኦሮሚያ ክልልን እንዲረዳና የኦሮሚያ ልማት ማህበር አማራ ክልልን አንዲረዳ ማስቻል
 21. የአማራ ነጋዴዎች የግል ድርጅቶችን በኦሮሚያ ክልል አንዲከፍቱ እና የኦሮሚያ ነጋዴዎችም የግል ድርጅቶችን በአማራ ክልል አንዲከፍቱ ማመቻቸት
 22. ከተለያዩ ብሄር የተወለዱ ወገንታዊ አቋም ለሌላቸው ምሁራን የአመራር ቦታዎችን መስጠት
 23. ከተለያዩ ብሄሮች የተወጣጡ ህፃናትና ወጣቶችን የሚያቅፉ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን (Boarding Schools) በየክልሉ ማቋቋም
 24. ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ምሁራንን ከራሳቸው ክልል ውጪ በሥራ በመመደብ ኢተዮጲያዊነትን ማጠናከር
 25. የመንግስትና የግል ሚዲያዎች የብሄር ለብሄር ትስስር ጉዳዮች ላይ በሰፊው ሥራ እንዲሰሩ ማድረግ…ለምሳሌ በጋብቻ

እስቲ እንማር

አንድ የፖለቲካ ፓርቲን እንደ አባት እንውሰድና ይህ አባት ሁለት ልጆቸ ያሉት ቢሆን፡፡ አነዚህ ሁለቱ ልጆች እርስ በእርስ ይጋጩበታል፡፡ እንደዚህ ሥርዓት ይህ አባት ቢሆን ኖሮ የበለጠ ግጭታቸውን በማጉላት ወንድማማችነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ይሞክራል፡፡ ጤናማው አባት ግን ችግሮቻቸውን በዕርጋታ በማዳመጥ  ይቅር እንዲባባሉ በማድረግ ወደ እርቅ ያመጣቸዋል፡፡