አባይ ሚዲያ ዜና

ረጅም ጊዜ የፈጀ ድርድር ከተደረገ ሀሃላ ከ45 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ከህዝቡ ጋር በመቆም ለነጻነት በሚደረገው ትግል ተሳታፊ ሆነዋል። ወያኔ በቅርቡ በተደረጉ ተደጋጋሚ ጦርነቶች ድል ፊቷን አዙራበት ለሽንፈት እየተዳረገ ይገኛል። በሰሜን ጎንደር የአማራው ህዝብ ከአገዛዙ ቅጥር ወታደሮች ጋር በሚያደርገው ፍልሚያ ድል እየቀናው ወያኔን ማርበደበዳቸውን ዛሬም ቀጥለውበታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰርጎ ገብቶ ከህዝቡ ጎን በመሆን ወያኔን እስከ ሞት ድረስ እየተጋደለ የሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር ወደ 46 የሚደርሱ ወታደሮች ከወያኔ መንጋጋ በመንጠቅ በከፍተኛና ጥንቃቄ በተሞላው የድርድር ሂደት ከተቀሩት የአርበኞች ግንቦት 7 ግንባር ሰራዊት ጋር መቀላቀላቸውን ግንባሩ ገልጻል።

እነዚህ 46 ወታደሮች ከሌሎች ምልምል ሰራዊት ጋር እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚሰለጥኑና የተጨቆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ቀንበር ለማላቀቅ በሚደረገው ትግል እንደሚሳተፉም ግንባሩ አሳውቋል። ወያኔን ከድተው ከህዝቡ ጎን ለመሰለፍና ፍጹም አምባገነናዊ የሆነውን የህውሃትን አገዛዝ ለመደምሰስ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 ግንባር የተቀላቀሉትን እነዚህን46 ወታደሮች በተመለከተ ወያኔ ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ሰአት ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም። ወታደሮቹ ወያኔ ያስታጠቃቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያቸውንም በመያዝ ከቀሪዎቹ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ጋር መቀላቀላቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በተያያዘ ዜናም በጎንደር በተለይም በሰሜኑ በኩል የሚደረገ ውጊያ እንደቀጠለና የአማራው ህዝብ በመደራጀት መሳሪያውን ሊነጥቅ የሚላኩትን የወያኔ ሰራዊትን እየተፋለመ ለነጻነት በሚደረገው ትግል የማይሻር አሻራ እያሰፈረ ይገኝል።