ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ ዘመን ተሻጋሪው ኮከብ


አባይ ሚዲያ
ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ ዘመን ተሻጋሪው ኮከብ
መስቀሉ አየለ

ከጥቂት ወራት በፊ እዚህ ግባ የሚባል እውቅና የሌለው አንድ መናኛ ሰው ነበር፤ ደመቀ ዘውዴ ። ያን ለማወቅ እንደ እርሱ የታሰሩትን ሌሎች አራት ኮሚቴዎች ማየት ነው። አሁን እንኩዋንስማቸውን በቅጡ የሚያውቃቸው ስንቱ እንደሆን አላውቅም። በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉም የሚያስታውሳቸው የለም። ነገር ግን ለምን የኮሎኔል ደመቀ ነገር በዚህ ፍጥነት የሚሊዮኖች አጀንዳ የሚሊዮኖች ማተብ ለመሆን በቃ። ምክንያቱ ግልጽ ነው። እርሱ እንደሌሎቹ እንደ በግ እየተነዳ አልሄደላቸውምና ነው። የቴዎድሮስ ልጅ ነኝ ፦እጀ ይፋጃል፦ ማለቱ ነው። ቴዎድሮስን ከመቶ አምሳ አመት ቦሃላ በቁመተ ስጋ እንድናየው ስላደረገን ነው። አዎ የወልቃይት ጉዳይ ከወልቃይት ሳይወጣ አርባ አመት ዋጋ አስከፈለ። የኮሎኔሉን ተጋድሎ ተከትሎ ግን አድማሳትና ቀላያቱን አጥልቅልቆ እልፍ አእላፍ ወትእልፊተ ምልፊት ሰዎችን አስከተለ። ዛሬ ይወልቃይት ጉዳይ በብርሃን ፍጥነት ከሳውዝ አፍሪካ እስከ ኖሮዌይ፣ ከካሊፊርኒያ እስከ ሲድኒ የማይጥሉት የማውጡት ትኩስ ድንች ሆነ።”ሽንታም” ብለው ሊሳለቁበት የሞከሩበትን ህዝብ ማንነት ያሳየ፣ የጎንደርን ሱሪ ያስመለሰና ነጫጭችባዎቹን የሴት ቀሚስና የሴት ኮንጎ እያለበሰ በጥይት የቆላው የህዝባዊ ተጋድሎው ምልክት ሆነ። በዚህም ኮሎኔል ማንነቱ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ተጣፈ። ሞት ህ ሞታችን ነው ተብሎለት ብዙ ወጣቶች በስሙ የሚሞቱለት አይዲዮሎጅ ሆነ እንጅ። ኢትዮጵያ እንደ አገር ከቆመችበት ግዜ ጀምሮ ለሽህ አመታት የኢትዮጵያዊነትን ግማደ መስቀል ተሸክሞ ለባእድ ወራሪና ከባንዳዎች ጋር ሲፋለም የኖረ በመሆኑ ከዘሩ ባሻገር እንደ አንድ ጠንካራ ህብረተሰብ በመውጣቱ በደረሰበት የመንፈስ ከፍታ የተነሳ ወደ ታች ወርዶ በዘሩ ማስብ አለመቻሉን እንደ ደካማ ጎን ወስደው በተፈጠረው ክፍተት ሲያደሙት የኖሩት የደደቢት አሪዮሳውያን ከእንግዲህ ስለቱ በማን እንደሚጸና ያዩታል።ለአራት አስርተ አመታት ሲገፋና ሲዳፈን የኖረው የኖረው የማንነት ቁጭት ዛሬ ፈንድቶ ወጥቷል። አንድ ግዜ የተጫነውን የዲንጋይ አለት ፈንቅሎ የወጣን የእሳተጋሞራ ከእንግዲህ በምንም አይነት ስሌት መልሶ ወደቦታው ማስገባት አይቻልም። ዛሬም ይወጣል ጀግና ከወልቃይት፤ እርፍ መጨበጥና ቃታ መሳብን እኩል የሚያውቅ፤ ሳይከፋው ገበሬ ሲከፋው ወታደር ሁሉን መሆን የሚቻለው መንፈሰ ብርቱ፤ ለሶስት ሽህ ዘመን እንደ አባይ ወንዝ ሲፈስ በኖረው የአባቶቹ የጀግንነት መንፈስ ጠላቶቹን ይደፍቃቸዋል። ከደደቢት የወጣውን ተናዳፊ እባብ አናት አናቱን ይቀጠቅጠዋል እንጅ ከእንግዲህስ አፈር ልሶ እንደገና ይነሳ ዘንድ እድል ከፊቱ አትቆምም።ዛሬ ድረስ ቋረኛው ቴዎድሮስን በልባችን አንግሰን ማኖራችን እንደሞት በመከበደው በዚያ ክፉ የጨለማ ዘመን አጥቢያ ኮከብ ሆኖ ብቅ በማለቱ ብቻ አይደለም፤ ቃሉን ጠብቆ ለማተቡ በማደሩ የገዛ ትንፋሹን እራሱ በመውሰዱ የተነሳ የቃልኪዳን የአንድነትና የጽናት ምሳሌ ስለሆነልንም ጭምር ነው እንጅ። የዛሬው ወልቃይቴ ደመቀ ዘውዴም እንድ ግዜ አርማችን ሆኖ ይቀጥል ዘንድ የታሪክ አጋጣሚ ከምንም አንስቶ የሰጠውን ይኽን ክብር ጠብቆ ያለፋል፤ በስሙ ሃውልት በስሙ ጽላት የሚቀረጽለት፤ በሚያልፍ ስጋውና መንፈሱን ደገኛ ታሪኩን ለዘላለም ትቶ የትናንቱን ቴዎድሮስ ታሪክ በዚህ ትውልድ ፊት ዳግም ህልው ያደርጋል፤ እንደ ቸኮቬራም የመታገያ አርማችን ሆኖ ይቀጥላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።ነገር ግን የዛሬዎቹ የራስ ሳሁለ ሚካኤል አልጋ ወራሾችም እጃቸውን በዚህ ጀግና ሰው ላይ ከማሳረፉቸው በፊት የአንድ ደመቀ ዘውዴ ዋጋውስንት ሚሊዮን የትግራይ ገዥ ጉጅሌ እንደሚያወጣ እንዲያሰሉት ደግመን ደጋግመን እናሳስባለን።