አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ

የወያኔ አገዛዝ 10,000 የሚሆኑ እስረኞችን መልቀቁን ቢያሳውቅም ከ70,000 ህዝብ በላይ በኦሮሚያ ክልል ታስረው እንደሚገኙ ተቋዋሚዎች ይፋ አድርገዋል።

አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደገለጹት ባሳለፍነው ጥቂት ወራቶች በኦሮሚያ ክልል ወያኔ ከ60,000 እስከ 70,000 የሚደርሱ ሰዎችን ወደ እስር ቤት አጉሯል።

እስር ቤቶቹ ከመሙላታቸው የተነሳ አንዳንድ መኖሪያ ቤቶችም ጌዚያዊ እስር ቤት በመሆን እያገለገሉ እንደሆነ አቶ ሙላቱ በማከል ለዚሁ ፕሬስ ገልጸዋል።

በመላው አገሪቷ የተቀሰቀሰውን የህዝብ እምቢተኝነትና ለህውሃት አልገዛም ባይነትን ተከትሎ የወያኔ መንግስት የአስቸኩዋይ ጌዜ አዋጅ ለማውጣት መገደዱ ይታወቃል።

አገዛዙን በመቋወም በአማራና በኦሮምያ ክልል ወደ አደባባይ በወጡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት ወታደራዊ እርምጃ ከ1500 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይታወሳል።