በአሶሳ በመንጌ ወረዳ በወያኔ ሰራዊትና በነፃነት ሃይሎች መካከል ከባድ ጦርነት ተካሄደ

አባይ ሚዲያ ዜና
አሰግድ ታመነ

በአሶሳ ክልል በመንጌ ወረዳ በሸረንቆል እንዲሁም በዳቡስ ማዶ 20 ቀን ባስቆጠረው ከባድ ውጊያ የነፃነት ሀይሎች ከፍተኛ ድል እያስቆጠሩ ነው።

ከ1000 በላይ የወያኔ መከላከያ ያለቀበት ሸረንቆሌና ዳቡስ ዛሬ ጥር 14 ቀን ድረስ የወያኔ መከላከያ እንደቅጠል ሲረግፍ መዋሉን ተነግሯል።

መራሹ የትግራይ መንግስት የደቡብ ተወላጅ የሆኑትንና የኦሮሞ የአማራ ተወላጅ የሆኑትን መከላከያዎች እየወሰደ እያስጨረሳቸው መሆኑን በስፋት እየተገለጸ ነው።

ወያኔ ከትግራይ ተወላጅ ውጭ ያለውን መከላከያ እየወሰደ እያስጨረሰው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ጥረት መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ወያኔ ህዝቡን ብቻ አደለም እያስጨፈጨፈው ያለው ከትግራይ ተወላጅ ውጭ ያለውን መከላከያም እያስጨረሰውና የጥይት ማብረጃ የፈንጅ ማምከኛ እያደረገው ይገኛል ።