48 ኢትዮጵያውያን በኬኒያ ወደ እስር ቤት ገቡ። የመኖሪያ ፍቃድ ባለመያዛቸው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ

ኬንያ ባሳለፍነው ሃሙስ መኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው አገሬ ላይ ሲንቀሳቀሱ አግቻቸዋለሁ ያለቻቸውን 48 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አሳውቋለች።

የኬኒያ ፓሊስ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ህገወጥ ስደተኞች ናቸው በማለት ለእስር ዳርጓቸዋል። 48ቱ ኢትዮጵያውያንም ሩሪሩ በሚባል የፓሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኝም መረዳት ተችሏል።

የኬኒያ ፓሊስ እነዚህን 48 ኢትዮጵያውያን  በዛሬው እለት (አርብ የካቲት 10 ቀን 2009ዓም) ለፍርድ እንደሚያቀርብ በኬኒያ የሚሰራጭ ማማ ራዲዮ የተባለ ጣቢያ ዘግቧል

በአፍሪቃ በትልቀቱ ቀዳሚ የሆነውን የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ እንዲዘጋ የኬኒያ መንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ከሁለት ሳምንት በፊት የአገሩ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

የኬኒያ መንግስት ስደተኞችን ተቀላቅለው የሽብር ቡድኖች አገሪቷ ላይ አደጋ ያደርሳሉ በማለት ቢከራከርም ፍርድ ቤቱ ለቡዙ ሺህ ስደተኞች መጠለያ የሆነውን የዳዳብን ካምፕ እንዳይዘጋ ውሳኔውን ማስተላለፉ ተዘግቧል።

በሶማሊያ ኢትዮጵያና ኬኒያ አልሸባብን ለመዋጋት ከፍተኛ ቁጥር የሆነ ወታደሮች ማሰማራታቸውም ይታወቃል።