የወያኔ ህወሃት ቀጣዩ ሴራ-ለወያኔ የተመቻቸው የሱማሌ ክልል አስተዳደር አመራር

 

ወያኔ ህወሃት ዛሬ ከፍተኛ ውጥረትና ኪሳራ ውስጥ ለመግባቱ አንደኛው ምስክር የመንግስት ፕሮፓጋንዳ፤ ልማት፤ እድገት፤ግድብ፤ባቡር ሰራሁላችሁ ሳይሆን አገር ማፍረስም እችላለሁ የሚል ቅዠት ማስወራትም ሆንዋል። ይህንንም ለህወሃት አገልጋይ በሆኑ ተቀጥላዎች በኩል እያናፈሱት ይገኛል።

በጅጅጋ ከተማ ባለፈው ጃንዋሪ፣ 2017 የሱማሌው ክልል ባለጌ አብዲ ማህሙድ ኦማር(አብዲ ኢሌይ) “ህወሃት ልገንጠል ካለ እኛም ተከታይ ነን” ማለቱ ይታወሳል። ይህን የተናገረው የተለያዩ በክልሉ የሚገኙ ጎሳዎችና፤የመንግስት ወታደሮች በተሰበሰቡበት ነው።

አብዲ ማህሙድ ኦማር(አብዲ ኢሌይ)ይህን ያገር ክዳት ሃሳብ ያቀረበው የህወሃት ጄነራሎች በተግኙብት ነው።ጄ/አብራሃም ወልደማርያም፤የሃረር እዝ ሃላፊ፤ጄ/ማሃሪ ዘውዱ፤ ሻለቃ ኢብራሂም ጃሊል ጋር በመሆን ነው።

“ትግሬዎች እንገንጠል ካሉ ከአማሮች ጋር መቆየት አንፈልግም” ባዪ አብዲ የተፈጥሮ ሃብታችንን ለአማሮች አናጋራም ባይ ነው።በዚሁ የምክክሩ ስብሰባ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠሉ የአዋጅ ረቂቅ የቀረበበት ሲሆን አብዲ ኢሌይ ከኦሮሞ በኩል የሚመጣብኝንም ወረራ መቋቋም እችላለሁ የሚልና ማእከላዊ መንግስት (ህወሃት ላልተቆጣጠረው) አልታዘዝምም ብሏል።

ብጅጅጋ የሚገኙት በጎሳ ምክክሩ የነበሩ ላይ የነበሩት እንደሚሉት ህወሃት የሱማሌን ክልል መንግስት የመገንጠልን ሃሳብ አጋዥ እንዲሆን እየገፋው ነው።

የወያኔ ህገ መንግስት፤አንቀጽ 39 ቁጥር(3) አንቀጽ 42 እና 47, 1994 መገንጠል የማንምና የሁሉም መብት አድርጎ ያስቀምጣል።የህዝብን ቁጥር፤የፖለቲካ ታሪክ ሁኔታን የሚመለክት አይደለም።አንቀጹ ያለው ገደብ ቢኖር የክልሉ ተወካዮች ይህን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናችው ብቻ ነው።

አሳዣኙ ሁኔታ ከሃያ አምስት ዓማታት የወያኔ ግዛት በኋላ አሁንም “አማራ በደለኝ” ብሎ ህወሃትን በማስተጋባት የሱማሌ ክልሉ መሪ መናገሩ ነው።

አባይ ሚዲይ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች ይህ የህወሃት መሰሪ የፖለቲካ እርማጃ እውን ሊተገብረው አይችልም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ብለው ይናገራሉ።በኢትዮጵያም የሚካሄደው አገር አድን በሄራዊ ትግሉ ከዚህ አፋራሽ የሆነው የወያኔ የፖለቲካ ፕላን ማመከንም ጋር የተዛያዘ ነው በለው ይናገራሉ።