አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ

የናዚው አዶልፍ ሂትለር ሲገለገልበት የነበረው ስልክ ለጨረታ ቀርቦ ለአንድ ግለሰብ መሸጡ ተገለጸ።

በሁለተኛው የአለም ጦርነት የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የተለያዩ ወታደራዊ ትእዛዞችን በቀጥታ ለጦር አዛዦቹ ይህንን ስልክ በመጠቀም ያስተላልፍ እንደነበረ ተዘግቧል።

በታሪክ እጅግ ክፉው ሰው ሲጠቀምበት የነበረው ዋና መሳሪያ በሚል ገለጻ ይህ ስልክ ለጨረታ ሊቀርብ ችሏል።

በተጨማሪም ይህ ስልክ የሂትለር የጥፋት ተልእኮ አቀጣጣይ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ የሚል ስያሜ በጨረታው አዘጋጆች ተሰጥቷታል።

የናዚ አገዛዝ ከወደቀ በሃላ የብርቲሽ ባለስልጣን የሆነው ብርጋዴር ራልፍ ራየን በ1945እኤአ ለጉብኝት በበርሊን ከተማ በተገኘ ጊዜ ይህ ስልክ እንደ ስጦታ እንደተበረከተለትም መረዳት ተችሏል።

ሂትለር ይህንን ስልክ የሚጠቀመው በዋናው ቢሮ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎዞ ላይም በመኪና በባቡር እንዲሁም በፊልድ ላይም ሲሆን የሚገለገልበት ተንቀሳቃሽ ስልክ ነበረ።

ማንነቱ እንዲታወቅ ያልፈለገ ተጫራች ይህንን የሂትለርን ስልክ በአንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ፓውንድ (£195,000)ወይም በ243,000 ዶላር ጨረታውን አሸንፎ እንደገው ተዘግቧል።

ሂትለር በሚሄድበት ባብዛኛው ቦታዎች ከአጠገቡ እንዳይለይ የሚፈልገው ብሎንዲ የሚባል ውሻ እንደነበረውም ይታወቃል።

በዚህ ጨረታ ላይም የሂትለር ውሻ ፎቶ ለሽያጭ ቀርቦ በሌላ ተጫራች በአስራ ዘጠኝ ሺህ አምስ መቶ ፓውንድ  (£19, 500) ተገዝቷል።