በአፍሪካ የቻይና የባህር ሃይል ወደብ ግንባታ አሜሪካንን አሳስቧል

አባይ ሚዲያ 

ጋሻው ገብሬ

ቤጂንግ ቻይና ከአገርዋ ውጭ ያላት የመጀመሪያዋ የጦር ካምፕ የአሜሪካ ከሆነው በጅቡቲ የሚገኝ የጦር ካምፕ በጥቂት ኪሎሜትር ብቻ የተራራቀ ነው።

ሁለቱ ሃያላን በደቡብ ቻይና ባህርም እንዲሁ አህጉር ለአህጉር ተመዘግዛጊ ሚሳይሎችን አጥምደው እየተፋጠጡ ናቸው። ምንም የሚያካልላቸው ወሰን በቦታው ባይኖርም በሳተላይትና በሳይበር(ኮምፕዩተር) አንዱ ሌላውን ሲሰልል ይቆያል።

አሁን በቅርቡ ደግሞ አሜኤሪካና ቻይና አጠገብ ላጠገብ ሆነው ጭው ያለው በረሃ ላይ ሊፋጠጡ ነው። ቻይና ዘመናዊ የሆነ በጅቡቲ ውስጥ ያለ የጦር ካምፕዋ ኻምፕ ለሞኔር ጥቂት ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ ነው የሚገኝ። ኻምፕ ለሞኔር የአሜሪካ መከላከያ ፔንታጎን ያሰራው በጣም ትልቁ የጦር ካምፕ ነው። ከቻይናው የጦር ካምፕ ቅርብ መሆኑ የአሜሪካን የጦር አመራር ጠበብቶችን የሚያሳስብ ሆንዋል። እንደ ችግር የታየው አሜሪካ በአረብ ባህር ሰላጤና ሰሜን አፍሪካ የምታደርገውን ጸረ ሽብር እንቅስቃሴ ቻይና በቅርብ ሁና ልትከታተል መሆኑ ነው።

አሜሪካ በጅቡቲ የሚገኝውን የጦር ካምፕ የገነባችው ትልቁ የሽብረተኛ ጥቃት ከደረሰባት ከሴፕተምበር 11 ቀን 2001 ዓ ም በኋዋላ ነው። ካምፕ ሌሞነር 4000 የጦር አባላትን የያዘ ነው። ካምፑ እጅግ ምስጢራዊ ዘመቻዎች የሚታቀዱበት ነው። መካከለኛው ምስራቅ፣ የአፍሪካ ቀንድን አካቶ ማለት ነው። ያለፈው ወር ፕሬዚዳት ትረምፕ ስልጣን አንደያዙ የመን ውስጥ በተደረገ ምስጢራዊ ዘመቻ ኔቪ ሲል ከሚባለው የአማሪካ ልዩ ጦር አንድ አባል መሞቱ ተነግሯል። ሞቱም አዲሱ መንግስት ላይ ወቀሳ እንዲቀርብ ማድረጉን የአሜሪካ ዜና አውታሮች ዛሬ እየዘገቡት ነው።

ሌላው አሜሪካንን የሚያሳስበው ጉዳይ ጂቡቲ በቻይና ከልክ ያለፈ ብድር መያዝዋ ነው። አሜሪካን እስከዛሬ ከጂቡቲ ጋር መልካም ግንኙነት ኖርዋት ቆይቶ ዛሬ ከፍያለው የቻይና ብድር ይህን ግንኙነት እንዳያበላሽ ስጋት አለ። የአሜሪካ ትኩረት የረጅም ጊዜ ዓላማቀፋዊ አክራሪ እስልምናን መዋጋት ነው።

ሮድ አይላንድ የተሰኘው የአሜሪካ ግዛት በሚገኘው የባህር ሃይል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ፒተር ዱቶን እንደሚሉት ይህ የቻይና በአፍሪካ ቀንድ በዚህ ሁኔታ መሰማራት ታላቅ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ነው። ቻይና የባህር ሃይሏን ማስፋፋትና በአካባቢው ያለውን ጥቅሟን መጠበቅ ነው ይላሉ። ቻይናም ክ200 ዓመታት በፊት ከነበረው የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ እየተማረችም ነው በማለት አክለው ይናገራሉ።

ዛሬ ቻያና በጅቡቲ 2400 ጦር አላት። ይህም በአፍሪካ ሰላም ጠባቂነት ያሰማራችው ነው። ቻያና አስከዛሬ 6000 ጀልባዎችን ከጥቃት አጅባ በኤደን ባህረ ሰላጤ እንዲያልፉ አድርጋለች፤ ዜጎችዋንም ከእገታ አድናለች። በ2011 ዓም ይህ ጦርዋ ከሊቢያ 35,000 ከየመን ውስጥ 600 ዜጎችዋን ከጥቃት አድናበታለች።

ቤሌላ በኩል የአሜሪካ ጦር ጠበብት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ሃይሏ አሳሳቢነቱ ላይ ግልጽ ባይሆኑም እንደ ስጋት የሚቆጥሩት አይደለም። ጠበብቱ እንደሚሉት እንዲህ ያለው የቻይና የጦር ካምፕ ጥቃትን ለመመከት አመቺ አይደለም።

ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ተንታኞች በአፍሪካ ቀንድ እየተከሰተ ያለውን የሀያላን አሰላለፍ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ዴሞክራሲያዊ ትግልና የአካባቢው አገራት ጥቅም ጋር አዛምደው እንዲያቀርቡት አባይ ሚዲያ ያበረታታል።