እገዳው ታገደ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
በሳምሶን ደበበ

የእስልምና ተከታዮችን የሚያግደው የፕሬዘዳንት ትራምፕ እገዳ በሃዋይ የፌደራል ዳኛ ታገደ

የመጀመሪያው የትራምፕ እገዳ በሲያትል ዳኛ እንደታገ እያለ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሌላ የማገጃ ትዛዝ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህ ሁለተኛ ትዛዝ ከመጀመሪያው ትዛዝ በጣም ያልተለየ ሆኖ በዛሬው ቀን በተግብር እንዲውል ተደርጐ የታዘዘ ነበር።

በተግባር ከመዋሉ ሰዓታት ቀደም ብሎ የሃዋይ ስቴት የፌደራል ዳኛ ትዕዛዙ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው ያገዱ መሆኑ ተውቋል።

ዳኛው ይህን ያዘዙት የትራምፕ እገዳ መሰረቱ እና አላማው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ለማገድ ያለመ በመሆኑና ይህ ደግሞ ከአሜራካ ህገ መንግሥት ጋር እንደሚፃረር ዳኛው ማስረጃዎችን ጠቅሰው አብራርተዋል።