ስደተኞች የጦር ቀጠናውን ሲወሩት ኢትዮጵያውያን ወደ የመን፤ የመኖች ደግሞ በሽሽት ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ይነጉዳሉ

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

የየመን ጦረነት ከፈነዳ ወዲህ 35,000 ስደተኞች ከየመን ወደ ጅቡቲ በተቃራኒ አቅጣጫ ደግሞ ፤10,400 ኢትዮጵያውያንና ሶማሊዎች ወደ የመን ተሰደዋል።

ኦቦክ በሰሜን ጂቡቲ ያለች ትንሽ ከተማ ናት። የሙቀትዋ ግለት 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው። የሞቀ አሸዋው ወጨፎ ይችን ወደብ ዘወትር ይመታታል። ኋላ ቀር ከተማ ናት። ቢሆንም ኦቦክ ከሁለት አቅጣጫ ለሚመጡ መንገደኞች መጠለያን ማረፊያ ናት።

በአንድ በኩል ከየመን የሚመጡ ስደተኞች ናቸው። የመኖቹ ኦቦክ የሚደርሱት 25 ኪሎ ሜትር በባብ ኤል መንደብ ተሻግረው ነው። በባብ ኤል መንደብ የእንባ በር ወይም የልቅሶ በር በመባል የሚታወቀው በአፍሪካ ቀንድ ያለ የባህር መተላለፊያ ነው።

በተቃራኒው አቅጣጫ ደግሞ ኢትዮጵያውያን በአገር አሻጋሪ ደላሎች ጀልባዎች ሆነው ወደ የመን ይጓዛሉ። ከየመን ወደ ጅቡቲ 35 ሺ ሰዎች ገብተዋል። ወደ ትንሽዋ በአምባገነን ገዢ ተዳዳሪ ከሆነችው ጂቡቲ። 35 ሺ በከፊል የመኒዎች ሲሆኑ የተቀሩት ሶማሊ ሰደተኞች፤ ወደአገር የሚመለሱ ጂቡቲያኖች እና ሌሎችም ናቸው።

ከእነዚህ ስደተኞ መካከል ሶማሊና ኤርትራውያን የሆኑት ወደ ሁላት ካምፖች ሲወሰዱ የመኒዎቹ ወደ ጂቡቲ ዋና ከተማ እንዲገቡ ይደረጋል። ይህንን እድል ያላገኙ መርቃዚ ወደ ተሰኝው ካምፐ ይገባሉ። ካምሲን በመባል የሚታወቀውን ቃጠሎ አቧራማ ሞቃት ንፋስን ይጋፈጣሉ። መርቃዚ የማይመች መሆኑን ለመግለጽ የሳውዲ እስር ቤት ይሻላል ይላሉ። ሆኖም የት ይኬዳል በማለት ስደተኞቹ ይችሉታል። የቆረጡ የመኖቹ ደግሞ ከዚህስ እዚያው ጦርነቱ ላይ መዋጋት ይሻላል በማለት ወደ አጋራቸው ይመለሳሉ።

የ ተ መ ድ የስደተኛ ተቋም ቢያስጠነቅቅም ወደ የመን የሚመለሱት ኢትዮጵያውያን እና ሶማሌዎችን የጫኑ የደላላ ጀልባዎች ናቸው። በ2015እኤአ ከተጓዙት 92 ሺ ሰደተኞች 90% ኢትዮጵያውያን ናቸው። በ2016 ሰደቱ ቀጥሎ 10 ሺ ተጨማሪ ተጉዘው የመን ገብተዋል። 65ቱ ደግሞ በጉዞው ላይ ሞተዋል።

ወደ የመን የሚሰደዱት ባብዛኛው ከኦሮሞ ብሄረሰብ ናቸው። ካሉበት የዘረኝነትና የጭቆና አገር ለማምለጥ ይህን ለመቶዎች አመታት መተላለፊያ የሆነውን መንገድ ለሽሽት ተጠቅመው ሳውዲ እና ሌላው አረብ አገር ታክሲ ነጂ፣ የእርሻ ሰራተኛ ለመሆን እደላቸውን ይሞክራሉ። እነህ ስደተኞች ሰለየመን የጦረነት ቀውስ ያውቃሉ። 6,400 የመኒዎች ሞተየዋል 2.8 ሚሊዮን ተፈናቅለዋል። ይህ ግን ኢትዮጵያውያኑን አያግዳቸውም። እንዲያውም በጦረነቱ ግርግር ሳንያዝ የምፈልገው ቦታ እንደርሳላንም ባይ ናቸው።

ተጓዦቹ ከኢትዮጵያ ድንበር ኦቦክ ለመድረስ ስላለው አራት ቀን የሚፈጅ በረሃ፣ ስለደላሎቹ ጭካኔ፣ እንዴት የመን ከደረሱ በኋላ በመያዣ ወላጅ ዘመዶቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲልኩ የሚጠይቁትን የደላሎቹ ክፋት ይናገራሉ። አንከፍልም ያሉ ለሞት ይዳረጋሉ። ገንዘባቸውን የተዘረፉት ባዶ እጃቸውን መንገድ ዳር ይወድቃሉ። በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንም እርድታ አያደርግላቸውም። ኢትዮጵያኑን ለዚህ መከራ የዳረጋቸው የወያኔ አገዛዝ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ወደ የመን ጉዞአቸው ቀጣይ ነው።