አርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት በሰሜን ኢትዮጵያ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ

አባይ ሚዲያ ዜና መርጋ ደጀኔ
 
 
የአርበኞች ግንቦት7 ሠራዊት በተለያዩ አቅጣጫዎች በስፋት ከሚያረገውን የማጥቃት ዘመቻ በተከታታይ ካደረጋቸው ጥቃቶች መካከል አንዱ የሆነ ጥቃት በደንቢያ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሟል።
 
በደንቢያና በአካባቢው በተደረጉ ውግያዎች የወያኔ መከላከያ ሰርራዊት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ እንደፈጠረበትና ሠራዊቱም የመዋጋት ፍላጎት እንደሌለው ይበልጡኑ ከነጻነት ሃሎች ጎን የመቆም ፍላጎት እንዳለው ከውስጥ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
 
በዚሁ ግንባር ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመው ይሄው ጥቃት በወረዳው ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ ሲሆን በአካባቢው የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ስብሰባ በማድረግ ላይ ነበሩ። በዚህ ጥቃት ምን ያክል የሰውና የንብረት ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም። የዓይን እማኞች እንደሚሉት ግን ጥቃቱ በነዋሪዎች ላይ ጉዳት አላደረሰም። በገዢው ፓርቲ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ በመፍጠሩ፣ ወታደሮች እርስ በርስ ሲወዛገቡ መታየታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
 
በሌላ አቅጣጫ በማክሰኚት አካባቢ ዳንጉላ ጭንጫዩ በሚባል ቀበሌ ላይ የአርበኞች ግንቦት7 ሠራዊትን ለማደን የሄዱ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች ያልጠበቁት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የድርጅቱ አመራሮች ተናግረዋል። አበበ ታከለ የተባለውን የታጣቂዎች መሪን ጨምሮ 3 ታጣቂዎች መቁሰላቸውንም ድርጅቱ በላከው ሪፖርት ገልጿል።
 
ከቀን ወደቀን ሽንፈትን በመከናነብ ላይ የሚገኘው የገዢው  መከላከያ ሠራዊት አሁንም የጠነከረ ብትር ከተለያዩ ግባሮች እየገጠመው ነው። ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት7 ሠራዊት የሚፈጽመውን ጥቃት አድማሱን እያሰፋ በመምጣቱ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት ከባድ የሞራል ውድቀት የደረሰበት ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ የገዥው መከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከተለያዩ ግባሮች ያላቸውን የሠራዊት ሃይል ወደ አንድ ግባር ለማሰባሰብ ተገደዋል።