የሜሂኮ የሃዋላ ገንዘብ ምንጭ ከየት ነው? ከኢትዮጵያ ሁናታ ጋር በምን ይመሳሰላል?

ከአገሩ በተሰደዱ ተወላጆች የሚደገፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሌሎች ምሳሌዎችም አሉ።አንዷ ምሳሌ የአሜሪካ አዋሳኝ የሆነችው ሜሂኮ ናት። እርግጥ ነው የሜሂኮ ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ በመጠን እጅግ ይራራቃሉ።የሜሂኮ ጠቅላላ የአገሪቱ ምርት $1143.79 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያ ደግሞ $61.54 ብቻ ነው። ይህ ጽሁፍ የሚመለከተው ካገራቸው የወጡ ዜጎች ካሉባቸው አገራት ሆነው የሚልኩት ገንዘብ ያገራቸው ምጣኔ ሃብት ይደግፋሉ የሚለውን ነው።ተጽእኖውን ባጭሩ ለማመላከት ነው።

የኢትዮጵያና የሜሂኮን ዝርዝር ከማየታችን በፊት ይህ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ገንዘብ ያለውን መንግስት አደጋ አፋፍ ደርሶ ማገገሚያው ወይም መንጠልጠያው መሆኑን ዛሬ እናያለን።ከ2016 ጀምሮ በተያያዘው ህዝባዊ አመጽ የተነሳ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው መዋእለ ንዋይ ምንጩ ደርቋል።የውጭ ኢንቬስትሮች በጣም ሰግተዋል።ያሉትም ፋብሪካዎች ከውጭ መለዋወጫ ማስገባት አልቻሉም።በመዳከምና መሽመድመድ መካከል ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዳይለይለት በነፍሱ እንደርሳለን ያሉት ሳዉዲ አረቦች ሊታደጉት ቃል ቢገቡም የሆነ ነገር ገና የለም።ታዲያ በዚህ ጊዜ ይህ በህዝቡ ላይ ግፍ የሚውል መንግስት ለመጣል በስደት ያለው ዜጋ የሚልከውን ገንዘብ መንግስት በማይደርስበት መንገድ ቢያደርግ ህዝባዊ ትግሉን መርዳቱንና የወያኔንም እድሜ ማሳጠሩን ማመላከት ተገቢ ይሆናል።

ሜሂኮ የዩናይትድ ስቴትስ የአሜሪካ ጎረቤት ናት።በሁለቱ አግሮች መካከል በስደተኞች የተነሳ ፕሬዚዳንት ትራፕ አቸናፊ በሆኑበት መርጫ ብዙ ተብሏዋል።ትራምፕ ከሜሂኮ ፈልሰው የሚመጡት ወንጀለኞች ናቸው። አገራችን መግባት የለባቸውም።እንዲያውም በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማገድ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወሰን አጥር አጥረበታሁም ሁሉ ብለዋል።

ከፖለቲካው ባሻገር ሜሂካኖች ወደ አሜሪካ የስራ እደል ፍለጋ መምጣት የጀመሩት ዛሬ አይደለም።በህጋዊነት ሆነ ህገወጥ ሆነው የሚኖሩት በአንድ ተግባራቸው ይመሳሰላሉ።ይህም ወደ አገራቸው ከሰሩት፤ ካፈሩት ገንዘብ ለዘምዶቻቸው ይልካሉ። ልክ ወደ አጋራችን ኢትዮጵያ ከውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢዮጵያውያን እንደሚያደርጉት ማለት ነው።

ገነዘቡ መጠኑ ትንሽ አይደለም።በ2016 ሜሂኮ $27 ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ በህዋላ ሜሂኮ አግኝታለች።ይህ ደግሞ አገሪትዋ ከነዳጅ ሃብትዋ ሽያጭ ከምታገኝው 18.7 ቢሊዮን ዶላር ሲተያይ በጣም የበለጠ ነው። ሜሂኮ ከአሜሪካ በ1996 $4.2, 2006 $25.5, 2016 $27 ቢሊዮን ዶልላር በሀዋላ አግኝታለች።

በቅረቡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ ወደ ሜሂኮ በሚሄደው ገንዘብ ላይ ቀረጥ እጥላልሁም ባይ ናቸው። አጥር አጥራለሁ ያሉትም የአጥሩ ክፍያ ገንዘብ ከዚህ ቀረጥ ስብሰባ ላይ ሊገኝ ይችላል ባይ ናቸው።የሜሂኮ መሪዎች ግን ይህን በፍጹም የማይቀበሉት ነው።

ሃዋላ ሜሂኮ ያለን ድህነት እጅግ አድርጎ ቀንሷል ባይባልም የረዳው ነገር አለ።በዚህ ሁኔታ ገንዘብ ከአሜሪካ ወደ ሜሂኮ ሲፈስ የጀመረው ከብዙ ዓመታት ጀምሮ ነው።በ1995 ሰፊ የንግድ ስምምነት በሜሂኮና አሜሪካ መካከል ተደርጓል በዚሁ ዓመተ ምህረት $3.6 ቢሊዮን ዶልላር ሜሂኮውያን ወደ እገራቸው ልከዋል።ባጠቃላይ የድህነት መጠኑ ቢቀንስም፤ በሜሂኮ ችግር አለ።በ1994 ዓም 9.2 ሚሊዮን የሜሂኮ ስዎች ድህነት ላይ የሚገኙ ናቸው።አላወቁም እንጂ ትራምፕ ነገሩን ባይነካኩት ያሰኛል።በሃዋላ ወደ ሜሂኮ የሚገባው ገንዘብ እፈልሳለሁ የሚለውን እዚያው ይይዝላቸው ነበር የሚሉ አሉ።ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያና ሜሂኮ ኢኮኖሚያችው ውጭ ከሚኖረው የዜጎች ድጎማ ተጽእኖ አይወጣም ማለት ነው።

የሜሂኮ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር በህዋላ ወደ አገር የሚገባው ገንዘብ ማንን ይጠቅማል? የሚለው ወሳኝ ነው።በሜሂኮ ገንዘቡ የሚላክለት ህዝብ ተጠቃሚ ነው።በኢትዮጵያ ግን ተጠቃሚው መንገስት ነው።የህወሃት ወያኔ መንግስት የባንኮች አሰራር ለራሱ እንዲያመች የሚቆጣጠር በመሆኑ ይህን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ለራሱ መጎልበቻ፤የቅንጦት እቃ ከውጭ አገራት ማስገቢያ ያደርገዋል።ዞሮም በሙስና ካገር እንዲወጣ ያደርገዋል።

የሜሂኮን ያህል ባይሆንም ይህ ከውጭ የሚገባው ገንዘብ ከራስዋ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር እጅጉን ብዙ ነው።የፒው ሪሰርች ማእከል አንደሚያሳየው 2015 ከአሜሪካ ብቻ $198,000,000 ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ገብቷዋል።ጠብ ያለ መሻሻል ግን የለም። በሚገባው ገንዘብ ሰው ከድህነት መውጣቱ በሜሂኮ በኩል በግልጽ ይለካል።ትንሽም ቢሆን ይደጎማል።የተጠቀመውም ማን ይሁን ይታወቃል።በኢትዮጵያ ግን መሻሻል ሳይሆን የጨመረ ድህነት የሚታይበት መንገድ ይታያል።በሚገባው ገንዘብ ተጠቃሚው ገንዘቡ የሚላክለት ህዝብ አይደለም ማለት ነው።ሌላው ችግር በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት የገንዘቡን ዋጋ መሸርሸሩ ነው።

የሜሂኮ ሃዋላ መንጩ አማሪካ ነው። የኢትዮጵያም ትልቁ ድርሻ የሚላከው ከአማኤሪካ ቢሆንም  ዓለም አቀፍነት መልክም አለው።በዓለም በመበተናችን ምከንያት መሆኑ ነው። እርግጥ የሜሂኮ ኢኮኖሚ  ከኢትዮጵያ ሲወዳደር እጅጉን ትልቅ ነው።ሜሂኮ የተፈጥሮ ሃብት ታድሎ ባስተዳደር ግን ብልሹ ነው።እንደ አገራችን ማለት ነው።የእጽ ነጋዴ ወንጀለኞች መረን የለቀቁብት፤ሙስናም የነገሰበት አገር በመሆኑ ለህዝቡ የስራ እድል ሊፈጥር ባለመቻሉ ሰው ወደ አሜሪካ መጥቶ መሸቀልን ይመርጣል።እድገት ለማግኘት ዞሮ ዞሮ ሰርቶ የሚያሰራ መንግስት፤ሰላምና፤ፍትህ የሚያሰፍን ስርዓት ቀድሞ መጠየቁ አይቀርምና።

ህዝብን በድሎ ንብረቱን እየዘረፈ፤እያስዘረፈ ያለ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ በያዋላ የሚገባው ገንዘብ ቢቋረጥበት የሚከተለውን የ ኢኮኖሚ ቀውስ ፍጥጽሞ አይቋቋመውም ይላሉ የምጣኔ ሃብት ጠበብት።ትንሽ የነዳጅ ዋጋ ጭማሬ እንኳን የዘውድ አገዛዝን ፍጻሜ የለኩሰች ክብሪት ተደርጋ በታሪክ ትነገራለች።