ከደባርቅ የመጣ የማስጠንቀቂያ መልእክት! ህዝቡ የወያኔ ማታለያ ትኬት እንዳይገዛ

ወያኔ ጎንደር ውስጥ ከዘጠኝ ወራት በላይ የቆየውን ህዝባዊ ትግል አቅጣጫ ለማስቀየር ከአሁን በፊት ተደርጎ የማይታወቅ እሩጫ ደባርቅ ከተማ ላይ ለማድረግ እየተንገዳገዱ ነው። ይህን የወያኔ ህዝብ ማታለያ ሩጫ ለመጋቢት 24 2009 ነው ለማዘጋጀት ያቀዱት።
ከደባርቅ የመጣው የማስጠንቀቂያ መልእክት ህዝቡ የወያኔ ማታለያ ትኬት እንዳይገዛ ይላል። ይኸውም ወያኔ ሆን ብሎ ደባርቅን ከሌሎቹ ከጎንደርና ከዳባት እንዲሁም ከባህርዳር ህዝቦች ጋር ለማለያየት እያደረገው እንደሆነ እንዲታወቅ፡፡


ሁለተኛ ፓርኩ ላይ የተሰራው ሎጅው ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚሠጠው ጥቅም አናሳ እንደሆነና ይህ ደባ ወያኔን ለማስተዋወቅ ራስ ደጀንንም ለትግራይ እንደመስጠት እንዲቆጠር ብለዋል።


ሎጅው በሚሊዮን እያስገባ ህ/ሰቡ ግን የሚጠቀመው ነገር የለም። የአክስዮን ድርሻው እንኳ በአዜብ መስፍን የአጎት ልጅ ስም ሆኖ ለእርሷ ለአዜብ ነው የሚገባው። አካባቢውን ያልጠቀመ ነው። እናም የሰሜንን ሰው ከወገኑ አማራው እና ከኢትዮጵያ ለማራቅ የተጠነሰሰ ስለሆነ ማህበረሰቡ ትኬት አለመግዛቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ተላልፏል።


ሃገራችን በሃዘን ድባብ ውስጥ ባለችበት ሰዓት አዚህ ሩጫ ማካሄዱ ወያኔ ደባርቅን ከሌላው ህብረተሰብ ጋር ለማራራቅ አየሠራው ያለ ሴራ መሆኑ እንዲታወቅ። ይኽውም ወገኖቻችን ቆሸ ላይ እንዲሁም በተለያዮ የአማራ ቦታዎች እየፈሰሰ ያለው ደም ሳይደርቅ እንደማንሮጥ ይታወቅልን ብለዋል። ይልቅ ይህን አጋጣሚ ወገኖቻችንን ለማሰብ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት አንደምናደርግ ይታወቅልን ብለዋል።


ሌላው የደባርቅ ህዝብ በጀግንነት ወገኖቹን ባጣበት ሰአት የሚደረገው ሩጫ ወያኔ የከሸፈ የፖለቲካ እስትራቴጅ እንደሆነ እንዲታወቅ። ህዝቡ ቀድሞ እንደማይሳተፍ በወሰነበት ሰዐት የወያኔ ተላላኪዎቹ ቤት ለቤት ትኬት ለመሸጥ መንከራተታቸው መጀመራቸው አስረጅ ነው፡፡


የአማራን ህዝብ ለመጨረስ የተደረገ ሴራ እንደቀጠለ ነው። በቅርብ በዳባት ወረዳ አጅሬ ጃኖራ ላይ በህፃናት ላይ የደረሰውን እናስታውሳለን። በአንድ የክትባት ብልቃጥ የተወጉት አስራ አራት ህፃናት የታመሙ ሲሆን አራቱ ወድያው እንዲሞቱ ሆኗል። ቆይቶ አምስተኛው ህፃን የሞተ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ በወቅቱም ህፃናቱን ህክምና ማድረስ አለመቻሉ ታውቋል።


ይባስ ብሎ ዳባት፣ አዲአርቃይ እንዲሁም ደባርቅ በአቶ አየልኝ ሙሉአለም የቀድሞ የአማራ ጤና ቢሮ ሃላፊ የአሁኑ የሠሜን ጎንደር አስተዳዳሪ በተጠነሰሰ ሴራ አማካኝነት የደባርቅ ሆስፒታል አገልግሎት ወደማይሰጥበት ደረጃ እንዲሸጋገር እያደረጉት ይገኛል። ሰራተኛውን በማስፈራራት በአንድ ወር ውስጥ ከሃምሳ በላይ ነባር ባለሙያ ከስራ እንዲለቅ ተደርጓል፡፡ ሰራተኞች ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ በሃላፊው በኩል የስድብ እንዲሁም ሃላፊው ቢሮ አስጠርቶ በጥፊ እና በቦክስ ይማታል።


ሆስፒታሉ በመዳህኒት እጦት ላይ መሆኑም ታውቋል ፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ሆን ተብሎ አካባቢውን ለመጉዳት እንደ እብድ የሚቆጥሩትን ከጠለምት ወረዳ በሙስና የተባረረ ሃላፊ በመመደብ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈፀመ ደባርቅ ላይ ወያኔ ያዘጋጀውን ሩጫ እናወግዛለን። ህዝባችንም ከዚህ የወያኔ ወጥመድ እራሱን ያግልል።