በባህርዳር በወያኔና በህዝብ መካከል ግጭት ተከሰተ ከ200 በላይ ወጣቶች መታሰራቸው ተነገረ

በትናንትናው ለት ባህርዳር  ከተማ ልዩ ስሙ ይባብ ካምፓስ በተባለው ቦታ ህገ ወጥ ቤቶች ናቸው በሚል  የከተማው መስተዳደር ከወያኔ ሰራዊት ጋር በመሆን የነዋሪዎችን 325 ቤቶች ማፍረሳቸው ተነገረ ።

በዚህም ምክንያት በከተማው ከፍተኛ ረብሻ የተነሳ ሲሆን ታጣቂዎች የከተማውን ህዝብ የደበደቡና ከ 200 በላይ ወጣቶች ማሰራቸው ተነግራል።

በድብደባው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች  ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ህክምና የተደረገላቸው መሆኑም ታውቃል።

በከተማው የወያኔ ታጣቂዎች ከፍተኛ ፍተሻ ያደረጉ ሲሆን ወጣት የባህርዳር ልጆችን እያደኑ በማሰር ላይ መሆናቸውም ታውቃል።


በባህርዳር ከተማ በአጠቃላይ 2700 ቤቶች ይፈርሳሉ የተባለ ሲሆን ትናንተ ምሽት ከክልሉ መስተደደር ቢሮ ለማነጋገር የሄዱ ቢሆንም  በአድማ በታኝ ፖሊስ መባረራቸውም ተነግራል ።