በብሪታንያ ለንደን ከተማ በሚገኘው ፓርላማ በደረሰ ጥቃት አራት ሰው ሲሞት ወደ ሀያ የሚጠጉ መቁሰላቸው ተነገረ

ለንደን የሚገኘው የብሪታንያ ፓርላማ ሕንጻ ዛሬ የተኩስ ድምፅ በመሰማቱ መንገዶች ተዘግተው ነበር።

የብሪታንያ የታችኛው ምክር ቤት መሪ ዴቪድ ሊንግተን በፓርላማው ሕንጻ ውስጥ ግጭት እንዳለ መዘገቡን ገልጸዋል። የብሪታንያ ባለሥልጣናት ሁኔታውን የሽብር ጥቃት ሊሆን ይችላል ብለውታል።


ነገሩ የጀመረው አንድ ኤስ.ዩ.ቪ የተሰኘ ተሽከርካሪ በፓርላማው አጠገብ ባለው ዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ብዙ እግረኞች ላይ ጉዳት ማድረስ ከጀመረ በኋላ ነው ተብላል።

የለንደን አምቡላንስ አገልግሎት ቃል አቀባይ ቢያንስ የአራት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል 20 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ተብላል ።


ከፖሊስ ምንጮች አንድ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንን በገለጹት መሰረት፤ “መኪናው በአሮጌው ቤተመንግሥት በር አከባቢ ሌሎች ሰዎችንም ተኩሶ መጣሉን ተናግረዋል የሞቱት እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችን ተነግራል።

ታጣቂው ወደ አሮጌው ቤተመንግሥት በር ለመግባት ሲሞክር በር ላይ ከቆመው ፖሊስ ጋር ይጋጫል ከዛም ደጋግሞ በቢላ ፖሊሱን ወጋው፣ በዛን ወቅት ሌሎች ፖሊሶች ተኮሱባት” ሲሉ የሀይን እማኞች ገልጸዋል።

17436044_1447109348653605_4417501000745963547_o17458224_1447109535320253_5871613432176306372_n