አጼ ዮሓንስ ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኤርትራውያንን ጨፍጭፈው ነበር- የታሪክ ማስረጃዎች

የዘንድሮው የአድዋ በዓል አከባበር ከፍተኛ ጽንፍ የታየበት ነበር :: ከፊሉ በዓሉን በድምቀት ሲያከብር ከፊሉ ደግሞ ሲያወግዝ ውሏል:: የተለያዩ አመለካከቶች በማህበራዊ ሚድያዊ ቢታዩም ፣ የዘንድሮው የአድዋ በዓል አከባበር ለየት ያለና በርካታ ውይይቶች የተካሄዱበት ነበር:: በተለያዩ ወገኖች ሲነሳ የነበረው አንዱ ነጥብ ” የኤርትራውያን ከጣልያን ሰራዊት ጎን በተለይም ከጀነራል አልበርቶኒ ጦር ጋር አብሮ ኢትዮጵያን መውጋት” የሚለው ምክንያት የጎደለው ሀሳብ ነበር :: እርግጥ ነው ኤርትራውያን ከጣልያን ሰራዊት ጋር አብረው ነበር ። ግን ለምን ? መልሱ የህልውና ጥያቄ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ስለነበር ነበር ። እንዲህ ላብራራው

 የኣጼ ዮሓንስና የራስ አሉላ ግፍ( genocide)በኤርትራውያን ላይ

በቀድሞ ስማቸው ካሳ (በኋላ አጼ ዮሓንስ) ስልጣን ለመያዝ ሲሉ በጀነራል ናፒየር የሚመራውን የንግሊዝ ጦር እየመሩ አጼ ቴዎድሮስን አስገደሉ ። ለዚህም ውለታቸው ( በስምምነታቸው መሰረት) ከጀነራል ናፒየር በርካታ የጦር መሳርያ ተበረከተላቸው:: በዚህም በመታገዝ የንጉሰ ነገስትነቱ ወንበር ላይ ቂጢጥ ባሉ ማግስት ፊታቸውን ያዞሩት ወደ ምድሪ ባህሪ ( ያሁና ኤርትራ) ነበር::

የኤርትራ ሕዝብ Victim mentality የማይሰማው ኩሩ ሕዝብ ስለሆነ ” እንዲህ ተበደልኹኝ” ብሎ በሙት ላይ ማልቀስ ስለማይወድ እንጂ አጼ ዮሓንስ ስልጣን ከያዙ ጀምረው ፣ ኤርትራውያንን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያልሰሩት በደል የለም:: እጅ ከምን መባሉ አይቀርምና ማስረጃዎቼን ላቅርብ ።

 የራስ አሉላ የጨፈጨፏቸው ሁለት መቶ ሺህ ኤርትራውያን ኩናማዎች

 ታዋቂዋ የህግ ምሁር ሊድያ ( Lydya) እና የዪንቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ ልሂቅ ፕሮፌሰር( Emeritus professor)  የሆኑት ዶክተር ሮይ ( Roy)  የተባሉ ምሁራን ባሳተሙት Blood, Land, and Sex: Legal and Political Pluralism in Eritrea በተባለው ዝነኛ መጽሃፋቸው ላይ ( ገጽ 36) ፤ አጼ ዮሓንስ በኤርትራ ዘመቻቸው ላይ ከኤርትራ ሕዝብ አንዱ የሆነው የኩናማ ብሔር “ እምቢ አልወረርም አልገዛም ”  በማለቱ በወቅቱ የነበረውን ኩናማ ሁለት ሶስተኛውን በአስከፊ ጭካኔ ጨፍጭፈውታል:: የወቅቱ የኩናማ ሕዝብ እንደ ምሁራኑ ገለጻ ፣ ሶስት መቶ ሺህ ሲሆን የዙህ ሁለት ሶስተኛ ማለት ያለቀው ኤርትራዊ ኩናማ ሁለት መቶ ሺህ ነበር:: page 36

“The most infamous of these raids was held by Ras Alula in 1886. It caused the extinction of two third of the Kunama and the Nara living in the North Gash region.”

ሁለት መቶ ሺህ ሰው በራስ አሉላ የተጨፈጨፈበት የኩናማና የናራ ሕዝብ ፣ ራስ አሉላን ሊወጋ ቢመጣ ይደንቅ ይሆን? ከጣልያንና ከራስ አሉላ ጨካኙ ጨፍጫፊ ማን ነበር? ፍርዱን ወገንተኛ ባልሆነ ሕሊና ለማይፈርድ እውነትኛ አንባቢ ትቼዋለሁ::

የኣጼ ዮሓንስ አስመራ መግባትና ሓማሴኖችን እጅ መቁረጣቸው እና አስመራን ማቃጠላቸው

 የአጼ ዮሓንስና የራስ አሉላ ጭፍጨፋ ጋሽ ባርካ ላይ ወይም ኩናማና ናራ ላይ ብቻ አላቆመም:: ቴዎድሮስን ለመግደል እንግሊዝን መንገድ በመምራታቸውና ምስጢር በማውጣታቸው ከጀነራል ናፒየር ተበረከተላቸውን፣ ሁልቆ መሳፍርት በሌለው ነፍጥ እየታገዙ አስመራ አልፎም እስከ ከረን ደረሱ:: አስመራ ላይ እንደደረሱ ማንም ሰው ከምጽዋ ጋር ንግድ እንዳይነግድና ለሳቸውም መጠኑ የሰፋ ግብር እንዲከፍልና የሓማሴና የሰራዬ መሬት አንድ አስረኛው የንጉሱ ለራሳቸው ስለሚፈልጉት እንደወረሱት አስታወቁ::

በዚህ የተቆጣው የአካለጉዛይ ሃማሴን እና መሰል ሕዝብ ፣ መራር ተቃውሞውን አሰማ:: በተለይም የሓማሴኑ ራስ ወልደሚካኤል ጦርነት ገጥመው አስመራ ላይ ከትሞ የነበረውን የአጼ ዮሓንስ ጦር ፈጀው:: አጼ ዮሓንስም ሃማሴንን አስመራን በተለይም የራስ ወልደሚካኤል ከተማን ሙሉ በሙሉ በሳት አቃጠሉት:: ሕዝቡንም እጁን መቁረጥ ጀመሩ:: Emeritues professor Roy ( Eritrea: even the stones are burning) በሚለው መጽሓፉ ገጽ 40 ላይ ሁኔታውን እንዲህ ይገልጹታል

“In 1873, Emperor John sent troops to occupy Hamasien ans Seraie. They so terrified the population… December 1875 the emperor appointed a new governor of Asmara. He attempted to prevent trade with Mitswa by penalizing … confiscation of their good for the first time and amputation of their hand for the second. By all accounts the inhabitants were unwilling to pay taxes and were in rebellious mood… in turn John ordered the destruction of the entire village of Asmara known to support the koraj. ..And Ras Alula during his brief period of rule as lord of Mereb Melaash, excluded all local (Eritrean) leaders from political life and attempted to confiscate ten percent of the land. He was fiercely and successfully opposed by the local inhabitants…. the Mensa ruling clans of the Western lowlands became Muslim as a reaction from the merciless raids of the Christian overlords of Tigray”

ከአድዋ ጦርነት በፊት አጼ ዮሐንስ ኤርትራውያን ላይ የሰሩት ግፍና በደል በጥቂቱ ይሄንን ይመስል ነበር:: ኤርትራውያን መነገድ አይችሉም ነበር:: ቢነግዱ ንብረታቸው ይወረሳል ቀጥሎም እጃቸው ይቆረጣል:: አልፎ ተርፎም ኤርትራውያን በሙሉ ከአመራር ቦታ ተወግደው በትግራይ ሰዎች እንዲተኩ ሆነ:: ይሄም አልበቃም አስር ከሞቶ የሚሆነው መሬታቸው ተወረሰ:: ይሄን ሁሉ ግፍ እምቢ ብለው ቢቃወሙ አጼ ዮሓንስ አስመራን እሳት ለኮሱባት::

ኤርትራውያን ጣልያንን ደግፈው አጼ ዩሓንስና ራስ አሉላ ላይ ቢዘምቱ ምን ይደንቃል? አሁንም ፍርዱን ለአንባቢ ትቼዋለሁ

ኤርትራውያንን መዝረፍና ማደህየት- የራስ አሉላና የአጼ ዮሓንስ ስትራቴጂ

 ኤርትራውያንን የሚደረግባቸው ግፍ ይሄ ብቻ አልነበረም:: ኤርትራውያን እንዳያንሰራሩና እንይነሱ በተለያየ ግዜ የራስ አሉላ ጦር እየወረረ ሕዝቡን ይዘርፍ ነበር:: አፍቃሬ ሕወሀት የሆኑት እስራኤላዊ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኤልሪክም Ras Alula and the scramble for Africa : A political biography : Ethiopia and Eritrea( ገጽ 35) በተባለው መጽሓፋቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል

“Ras Alula pillaged Tigre people in Keren and Sahil areas, taking “7,000 to 8,000 sheep and goats, almost as many cattle, and some 15000 Thalers (Maria Theresa dollars)”

በራስ አሉላ ዘመን የነበረውና ባይኑ ያየውን የጻፈው እንግሊዛዊው እንዲህ ሲል ፍንትው አድርጎ ያስቀምጠዋል (My Mission to Abyssinia ገጽ 245)

“When Portal passed through it, it contained a garrison of around two hundred of Alula’s soldiers who “behaved with great hauteur and even brutality to the Arab inhabitants”. “The land, not the people” was the underpinning approach to the “Eritrean problem” of successive Ethiopian regimes in the mid- and late twentieth century: such an approach is evident in the age of Yohannes and Alula. Indeed, Alula’s occupation of Asmara demonstrates part of the same strategy (Richard Reid, P. 245)

ከላይ በተለያዩ ማስረጃዎች አንዳየነው የራስ አሉላና የአጼ ዮሓንስ አስተዳደር ፣ ኤርትራ ላይ የፈጸመው በደል ሕዝቡን ክፉኛ አስመርሮት ነበር:: ማስመረር ብቻ ሳይሆን ኤርትራውያን ሕልውናቸው አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ነበር:: በራስ አሉላ እና አጼ ዮሃንስ ጨካኝ አገዛዝ የተማረሩ ኤርትራውያን ጣልያንን ለመቀላቀል ብዙ ጉትጎታ አላስፈለጋቸውም:: የሚፈልጉት ዘመናዊ መሳርያ ታጥቆ ዘራቸውን ለማጥፋት ና ኤርትራን ለመሸጥ ብዙ የደከመውን የራስ አሉላን ጦር መግጠም ነበር::

ራስ አሉላ ኤርትራን ለጣልያን እንዴት እንዳስማሟት

ኤርትራውያን አንዱ ቅያሜያቸው ፣ አስተዳደራዊ በደልና ዘር ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የመሬታቸውም ህልውና ጉዳይ ነበር:: በግዜው ኤርትራን በኃይል ይዘው ያስተዳድሩ የነበሩት አጼ ዮሃንስና ራስ አሉላ ኤርትራን ከጣልያን ጋር መወዳጃና መታረቂያ አድርገዋት ነበር:: አልፎ ተርፎም ራስ አሉላ ” የኤርትራ ገዥ እኔ ስለሆንኩኝ እኔ ኤርትራን ልስጣችሁ እናንተ ወዳጅ ሁኑኝ ” ሲል ተማጽኖ ለጣልያን አቅርበው ነበር:: አሁንም አፍቃሬ ህወሀት የሆኑት እስራኤላዊው ፕሮፌሰር ሃጋይ ኤልሪች Ras Alula and the scramble for Africa : A political biography : Ethiopia and Eritrea( ገጽ 164)ላይ የአሉላን ልምምጥ እንዲህ ሲሉ አስፍረውታል

 “You want the country to the Mareb (Eritrean highlands/Medri Bahri) to cultivate your gardens, to build your houses, to construct your churches….? We can give it to you. [And not Menilek.] Let the Italian soldiers come to Adwa, I shall come to meet them like a friend.” (1996, Ḥagai Erlikh, P. 164)

Ras Alula desperately continued to solicit the Italians, confirming that they can occupy all the lands up till the Mereb River, which is the historical and modern border between the Biher-Tigrinya of Medri Bahri/Eritrea and Tigrayans of Tigray/Ethiopia.

“And you (Italians), why do you need to look for distant friends? We are neighbors (meaning Medri Bahri and Tigray) and can serve each other. You want the road to be open and I want the road to be open. You should guard to the Mereb River and I will guard it to Gondar and even beyond Gondar. We must be able to go to the coast to trade in order that our country (meaning Tigray) would flourish, with the help of God; Menelik is too far to be of any use to you. Let us make friendship between us. (1996, Ḥagai Erlikh, 164)”

እንግዲህ እውነታው ይሄን ይመስል ነበር:: እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንደ አንድ ኤርትራዊ ቆጥረን ፣ በግዜው የነበርን ሰዎች ብንሆን ምን እናደርግ ነበር ብለን እንጠይቅ:: ያለምንም ጥያቄ ኣጼ ዮሃንስና ራስ አሉላን መፋለም ግድ ይላል:: ለህልውናቸው ለማንነታቸው ሲሉ ኤርትራውያን የራስ አሉላን እብደት ማስቆም ነበረባቸው:: ይህንን ክፍተት ያወቀውም ጣልያን ኤርትራውያንን አነሳስቶ ብዙ ኤርትራውያን ወታደሮችን መመልመል ቻለ::

በራስ አሉላ እጃቸው የተቆረጠው 800 ኤርትራውያን የአድዋ ምርኮኞች

በአድዋ ጦርነት ወቅት ፤ የበርካታ ኤርትራውያን ወታደሮች ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ማጥቃት አልነበረም:: ዋናው ህልም ዘራቸውን ያጠፋውን ራስ አሉላንና ሰራዊቱን መበቀል ነበር:: በአድዋ ጦርነት የጣልያን ጦርም ሲሸነፍ ከማንም በላይ እጅግ ሰቅጣጭ ፍርድ የተፈጸመውም ኤርትራውያን ምርኮኖች ላይ ነበር:: በራስ አሉላ ትዕዛዝ: 800 ኤርትራውያን ምርኮኞች እጃቸውና እግራቸው እንዲቆረጥ ሆነ:: በሓርቫርድና ዪንቨርስቲ ኦፍ ዋቪንግተን የታሪክ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሬይኖልድ ጀምስ ባሳተሙት መጽሓፍ( The Battle of Adwa ላይ ገጽ 235) ሁኔታውን እንዲህ ይተርኩታል

” Ras Alula .. Articulated this best in a remark he made to Askari taken prisoner after Amba Alagie. He said “You are Abyssinian, you have an emperor, and yet you have sought another king

of Italy. You are fighting against your brothers. For that i will punish you and i will cut off your hands”

ከላይ እንደተመለከትነው አጼ ዮሓንስ አስመራ እንደገቡ አንዱ አዋጃቸው ” እምቢ ያለውን እጁን እቆርጣለሁ” ነበር:: እንዳሉትም በርካታ እምቢ አንገዛም ያሉ የሓማሴና ሰራዬ ተወላጆችንን እጆች ቆርጠዋል:: በዚህ ተማረው ከጣልያን ጋር ሆነው ራስ አሉላን ለመውጋት የመጡትና የተማረኩ ኤርትራውያን ወታደሮችም አሁንም በራስ አሉላ እጃቸውንና እግራቸውን ተቆርጠው ይህ ነው የማይባል ግፍ ተፈጸመባቸው:: በነገራችን ላይ ተማርከው የነበሩት ጣልያኖች በሙሉ ተለቀው በሰላም ወደ ሮም ገብተዋል::

አጼ ዮሓንስ እና ራስ አሉላ በሌላው ዓይን ጀግና ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለኤርትራዊ ግን መራር ጠላት ናቸው!

የኣጼ ዮሓንስ የልጅ ልጅ ራስ ጉግሳ አሳልፎ የሰጠቸው የኤርትራ አርበኞች

 ኤርትራውያን ፤ የራስ አሉላና አጼ ዮሓንስን የግፍ ቀንበር ለመስበር በሚያደርጉት ትግል ፣ ትልቁን እንቅፋት  የነበረው ዘመናዊ መሳርያ እጦት ነበር:: የኣጼ ዮሓንስ ፣ ቴዎድሮስን መርተው በማስገደላቸው የተበረከተላቸው በርካታ ዘመናዊ መሳርያዎች ብዙ ውጊያዎች ላይ የበላይነትን አቀዳጅተዋቸዋል:: ስለዚህም ጦራቸውን ለማሸነፍ ዘማናዊ መሳርያ የግድ ነበር:: ለኤርትራውያን ደግሞ ይህን ማግኘት የሚችሉበት አንዱና ብቸኛው መንገድ ከጣልያን ስለሆነ ከጣልያን ጦር ጋር አበሩ እንጁ ፤ በርካታ ኤርትራውያን ኢትዮጵያን የመውጋት ፍላጎት አልነበራቸውም:: እንደውም ብዙዎቹ ጣልያንን እየከዱ ኢትዮጵያ ጦር ገብተዋል:: የሚገርመው ግን ፣ ምንም እንኳን የኤርትራ ጀግኖች ጣልያንን እምቢ ብለው ለኢትዮጵያ ሊዋጉ የጣልያንን መሳርያ ዘርፈው ኢትዮጵያ ቢገቡም – የትግራይ ገዥ ከነበረው  ከአጼ ዮሓንስ የልጅ ልጅ ራስ ጉግሳ የገጠማቸው ነገር ለአንባቢ የሚገርም ነው:: ደጃችማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ ራሱ ለጣልያን ባንዳ ስለነበረ – ከድተው የመጡትን ኤርትራውያን በሙሉ ከቦ መሳርያቸውን ዘርፎ እንዲታሰሩ ሆነ:: http://books.good-amharic-books.com/italy-3.PDF ቀኛዝማች አቋ ሰለባ ስብቻ 13,500 ጠመንጃ ነበር ይዘው የገቡት::

የአጼ ዮሓንስ የደም ግብር ወራሽችዋ ህወሀት የገደለቻቸውና የዘረፈቻቸው ኤርትራውያን

 የባድመው ጦርነት ወቅት፣ አቶ መለስ በቴሌቪዝን ላይ ወጥቶ ” ኤርትራውያንን ያይናችሁ ቀለም አላማረንም ብለን እናባርራለን” ሲል ብዙ የውጭ ዜጎችና ሌሎችም ተገርመው ነበር:: https://www.youtube.com/watch?v=IoAn7n5Bfq0 ጦርነቱ የነበረው ባድመ ላይ ነው:: የሚዋጋውም ውታደር ነው:: ግን ሰለባ የሆነው ኤርትራዊ የሆነ እና ኢትዮጵያ የነበረ ወገን ነው:; ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከሰማንያ ሺህ በላይ ኤርትራውያን ያይናችሁ ቀለም አላምረንም እየተባሉ ተባረሩ:: ንብረታቸው ተዘረፈ:: የህወሀት ባለስልጣናትም ከበሩበት:: ልቢ ትግራይ !!!! https://www.facebook.com/ethioamtv/videos/615027495336536/?fallback=1

ይሄ ለብዙዎች ኤርትራውያን አልገረመንም:: ምክንያቱም አሁን የተጀመረ አይደለም:: ከላይ ነካ ፣ ነካ ለማድረግ እንደሞከርኩት ከጥንት ከነ ራስ አሉላ ጀምሮ የነበረ በነ አጼ ዮሓንስ ዘመን ጀምሮ ሲፈጸም የነበረ ግፍ ነው::: ጥንትም መረብን ተሻግረው የኤርትራውያንን እጅ ሲቆርጡ ንብረት ሲዘርፉ ነበር:: አሁንም የተደገመው ያ ነው:: የነ ራስ አሉላና አጼ ዮሃንስ ውርስ መሆኑ ነው::

ሰሞኑንም አሻንጉሊቱ አቶ ኃይለማርያም ኤርትራ ላይ የአቋም ለውጥ መደረጉን ባደባባይ ተናግሯል:: ለህወሀት ቅርብ የሆነው ስም ክፉው ጋዜጠኛ ቢንያም ባደባባይ እንደተናገውም ” ኤርትራን አየር ኃይላችን ወይም ሌላ ኃይል ሄዶ ይድደብድብ ” ሲል ጦርነት አውጇል:: ጌታዋን ያመነች በግ ላቷን የትም ታስቀምጣለች እንዲሉ- ቢንያም ይሄን ከራሱ አላለውም:: ” ይሄን ተናገር” ብሎ የልብ ልብ የሰጠው አካል አለ:: ያም ህወሀት ናት:: ዳግም ጦርነት ዳግም እልቂት እይደገሰች ይመስላል::

ኤርትራ ከጥንት ጀምሮ በርካታ ግፎችን አስተናግዳለች:: ሕዝቡም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ስለሚያስቀድም ለሰላምና አብሮ ለመኖር ሲል በደሉን ውጦ እየኖረ ነው:: ይሄ ያለተዋጠለትን የህወሀት መንግስት ግን ጦር ያለሽ በዳቦ እያለ ነው:: እርጠና መሆን የምችለው ግን አንድ ነገር ነው::

” እንዲህ ዳምኖ ዳምኖ የዘነበ እንደሆን….”

         ከፍል ሁለት ይቀጥላል

ዋቤ

  1. https://www.facebook.com/ethioamtv/videos/615027495336536/?fallback=1
  2. http://books.good-amharic-books.com/italy-3.PDF
  3. The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire, Raymond James
  4. https://www.youtube.com/watch?v=IoAn7n5Bfq0
  5. Ras Alula and the scramble for Africa : A political biography : Ethiopia and Eritrea , Haggai Elrich
  6. Eritrea: even the stones are burning ,Roy
  7. Blood, Land, and Sex: Legal and Political Pluralism in Eritrea