የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተለቀቁ

አባይ ሚዲያ ዜና

መርጋ ደጀኔ

እኤአ የ2011 የአረቦች ዓመፅ ተከትሎ ለስድስት ዓመታት በእስር ቤትና በሆስፒታል የቆዩት የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ተለቀዋል። ሙባረክ ከነበሩበት ወታደራዊ ሆስፒታል ዛሬ ዓርብ መውጣታቸውን ቪኦኤ ገልጻል።

ሙባረክ በአረብ ሃገሮች ከተዛመተው አመጽ ተከትሎ ለፍርድ የቀረቡ ብቸኛው መሪ ሲሆኑ ለአስራ ስምንት ቀናት በዘለቀው አመፅ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ግድያ እንዲፈፀም አነሳስተዋል ተብለው የተከሰሱ ሌሎችም ክሶች ከተመሰረተባቸው በኋላ ውድቅ ተደርጓል፡፡ በቅርቡም ከግድያው ክስ ነፃ ተብለው ተበይኖላቸዋል።
ዛሬ የተለቀቁት ሙባረክ በአሁኑ ውቀት ሄሊዮፖሊስ በሚባለው የባለፀጎች ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እያረፉ መሆናቸውን ጠበቃቸው አረጋግጠዋል።