በፐርዝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ እጅግ በሚያመረቃ ሁኔታ በስኬት ተጠናቀቀ

አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም

በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ በተጠራው ስብሰባ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና የካውንስሉ መመሕር የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ለተሰብሳቢው ወቅቱ ሚጠይቀውን ተጨባጭ ሁኔታ አብራርተዋል

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በተጨማሪም በአሁን ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 በመሬት ላይ እያካሄደ ያለውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በስብሰባው ላይም የተገኙት ኢትዮጵያውያኖች በአገራችን ስላለው የፖለቲካና ሁነታ እና  እርበኞች ግንቦት 7 እያከናወነ ስላለው ትግል ያልተረዱትን እና ግልፅ ያልሆነላቸውን በመጠየቅ የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከስፍራው ለመረዳት ተችሏል።

በዚህ እኔ ለነፃነቴ በሚል መርሐ ግብር የአለም አቀፉ አካል ሆኖ የተዘጋጀው የድጋፍ ጥሪ በፐርዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በውይይቱ ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ በተጨማሪም ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ አስፈላጊውን እርዳታ እንዳደረጉም ታውቋል።

የወያኔ ጉጅሌው ህወሓት ከአገራችን ተወግዶ በምትኩ ሰላም፤ እኩልነት፤ ፍትህ፤ ዲሞክራሲና አንድ የሆነች ኢትዮጵያ እስክትገነባ ድረስ የሚጠየቁትን አገራዊ ግዴታ በመቀበል ለታጋዮች የሚያስፈልገውን ትብብር እንደሚያደርጉ ተሰብሳቢዎቹ አረጋግጠዋል።

የዚህ አለም አቀፍ እኔ ለነፃነቴ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በሚቀጥሉት ሳምንታት በብሪዝበን እና በሜልበርን እንደሚቀጥልም ታውቋል።

በብሪዝበን እና ሜልበርን ያሉት አስተባባሪዎችም ለዝግጅቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው የገለጹ ይገኛሉ።

በተለይ በብሪዝበን ለዚህ አኔ ለነፃነቴ ዘመቻ የወር ደሞዛቸውን ለመልቀቅ የተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያሳያል።