ዩ ኤስ አሜሪካ በመካከለኛው አፍሪካ ኤል አር ኤ ( LRA) ላይ የምታደርገውን አሰሳ አቆምኩ ብላለች

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

ዩ ኤስ አሜሪካ በመካከለኛው አፍሪካ ሎርድ ሬዚዝስታንስ አርሚ ወይም ኤል አር ኤ (LRA) በመባል በሚታወቀው ሽብርተኛ የጦር ድርጅት ላይ ስታካሂድ የነበረውን ዘመቻ መሰረዝዋን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ኤል አር ኤ ዮሴፍ ኮኒ በተሰኘው እስከ ዛሬ ድረስ ሊያዝ ባልተቻለው አመጸኛ የሚመራ ድርጅት ነው። የአሜሪካው ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን የዘመቻው መቋረጥን አስመልክቶ የሰጠው ምክንያት ዛሬ ኤል አር ኤ አቅሙ ከዚህ ግባ የሚባል ስላልሆነ ነው ብሏዋል።

ዮሴፍ ኮኒ በ2005 በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በጦር ወንጀል የዓላም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተበይኖበት የበረ ነው።

በ2010 አሜሪካ አንድ መቶ የሚሆኑ ምርጥ የጦር ሰራዊትዋን አካባቢው ካሉ የመንግስታት የጦር ሃይሎች ጋር በመሆን ኮኒን እንዲያድኑ አሰማርታ ነበር።

የአማኤሪካ ስለላ እንደሚለው ዮሴፍ ኮኒ ዛሬ ጤናው ታውኮ ይገኛል።ሰራዊቱም በክደት ምክንያት መንምኗል።

ኤል አር አኤ ( LRA) ከ1987 አንስቶ  አስከ አሁን የ100, 000 ሰዎችን ነፍስ አጥፍቷል። 60,000 ህጥጻናትን ከወላጆቻቸው ነጥቆ ወደ ሰራዊቱ አስገብቷል።

ከነዚሁ የህጻናት ተዋጊዎች መካከል አካለመጥን እስኪደርስ የተዋጋው ዶሚኒክ ኦንግዌን በሄግ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ዶሚኒክ በ2015 በአሜሪካ ጦር ሃይሎች በቁጥጥር የዋለ ነው።