የኬንያ መከላከያ ሰራዊት 31 የ አል ሸባብ አባላትን ገደልኩ ብሏዋል

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

ወያኔ ህወሃት የገዛ ህዝቡን ሲወጋና በደቡብ ሱዳን በኩል ድንበሩን ደፍሮ ለሚመጣ ሽፍታ ክፍት ሲያደርግ የጎረቤት አገራት የጦር ህይሎች ሽበርተኛ ን እየተዋጉ ነው።

————-

ዛሬ ማርች 27 ቀን የኬንያ መከላከያ ሰራዊት በሰጠው መግለጫ በሶማሊያ ባድ ሃሬ አካባቢ 31 የአል ሸባብ አባላትን መግደሉንና ቁጥራቸው በረካታ የሆኑ ደግሞ ማቁሰሉን እንዲሁም ሁለት ወታደራዊ ካሚዮኖች ማውደሙንም ገልጾአል።

የመከላከያ ሰራዊቱ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዮሴፍ ኦዊዎት በውጊያው ከባድ መሳሪያና ከሄሊኮፕተር ላይ ሆኖ የሚተኮስ መትረየስንም ጥቅም ላይ እንደዋለ ጸዋ

ወጂር አጠገብ 17 ኪሎሜትር ከሳሪራ አካባቢ የአልሸባብን የስንቅና የትጥቅ ዋና ካምፕ መምታቱን ዘርዝሯል።

ቃል አቀባዩ የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ሽብርተኞችን እያሳደደ ሶማሊያን ለማረጋጋት እየሰራ ነው  በማለት አስተያየታቸውን አክለዋል።

ኩልቢ በሚባል ቦታ ላይ በኬኒያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከሁለት ወራት በፊት በአፍማዶው በሚባል ቦታ የኬ መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ  57 ሽብረተኞች መገደላቸውን አስሰዋ

አል ሸባብ ከኬንያ ሌላ የዩጋንዳን፤ቡሩንዲንና የኢትዮጵያንና የጦር ካምፖች እየውረረ ከፍተኝ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።

ሶማሊያ አምባገነኑ ዚያድ ባሬ ከተወገደ በኋላ የተረጋጋ መንግስት ኖረዋት አያውቅም። የሸርና ጎሳ መስቅልቅል ያወካት አገር ናት።