አባይ ሚዲያ ዜና
አሰግድ ታመነ
በሰሜን ጎንደር በለምነታቸው የሚታወቁትን የአማራ ቦታዎች ለምሳሌ ወልቃይት፣ ሑመራ፣ ጠለምትና ጠገዴ የመሳሰሉትን የህወሓት ወያኔ ስርአት ወደ ትግራይ ክልል የማካለሉን ተግባር እየቀጠለበት እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።
ቦታውን የወያኔ ባለስልጣናት በመቆጣጠር ከፍተኛ ሀብት ያጋበሱበት ሲሆን ይህም ሳይበቃ በገዳምነት ለረጅም ጊዜ የሚታወቀውን የዋልድባን ገዳም ስኳር ፋብሪካ ይገነባበታል በሚል ታሪካዊውን ገዳም በማፈራረስና የገዳሙ ነዋሪ መለኮሳትም እየተዋከቡና ለእስር እየተዳረጉ እንደሚገኙም በተለያዩ ጊዜ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህንንና በማን አለብኝነት ቦታውን ወደ ትግራይ ማካለሉ ያስቆጣቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ትጥቅ ትግል በመጀመር የወያኔ ሀይል ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሆነ ተዘግቧል።
በአካባቢው ከፍተኛ የጥጥ ምርት እየተመረተበት እንደሆነ የገለጹት ምንጮች የህዝብ ሀይሎች ተለቅሞ ሊጫን የተዘጋጀ 440 ኩንታል በላይ ጥጥ ሙሉ በሙሉ ማውደማቸው ተነግሯል።
የእሳት ቃጠሎው የደረሰው መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ.ም እኩለ ቀን እንደሆነ የዐይን ምስክሮች ገልፀዋል። የወያኔ ባለስልጣናት የወልቃይትን ሕዝብ ሀብት እየቀሙ ባፈሯቸው ንብረቶች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ወደፊትም ሊቀጥል እንደሚችል ብዞዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።