አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ህልውናው አደጋ ሲሸተው የስልጣን ወንበሩ ሲንገራገጭ የሚስባቸው ቀይ ካርዶች

አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ህልውናው አደጋ ሲሸተው የስልጣን ወንበሩ ሲንገራገጭ የሚስባቸው ቀይ ካርዶች

ናትናኤል መኮንን

የህወሃት የዘረኝነት የጥጋብ ቁመና በህዝባዊ እምቢተኝነት ጡጫ ሲደቆስ ፣ የህወሓት በደም የጨቀየ እጂ በህዝባዊ አመፅ ሲሰባበር በተለያየ ጊዜ የስልጣን ወንበሩ ሲንገራገጭ ና ህልውናው አደጋ ሲሸተው ህጋዊ ሽፋን ያላው ቀይ ካርድ ይመዛል ።

ህግ በራሱ በህግ አውጭው በማይከበርባት ኢትዩጲያ እንደ ቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ ያሉ ህጋዊ ሽፋን የተሰጣቸው እጂግ ብዙ ለመቁጠር የሚታክቱ ህጎች ወጥተወል ምናልባትም ህግ አውጭና ህግ አስፈፃሚ ነኝ የሚለውን አምባገነን ቡድን እስካላስቆምነው ድረስ ነገም ይወጡ ይሆናል። የፀረ ሽብር ፣የፕሬስ …የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ (ወታደራዊ ዕዝ) ተጠቃሾች ናቸው ።

ለህወሓት ዘረኛ ቡድን የደም ስር የሆነው ዶላር በስደት የሚኖሩ ኢትዩጲያውያን የግድ አስቸኳይና አስፈላጊ ካልሆነ ወያኔ እንዳይደርሰው በማድረግ እንዳይልኩ በተነጋገሩበት ማግስት ለከፍተኛ የዶላር ምንዛሬ እጥረት መመታቱ በአንደበቱ ሲንተበተብ ከመስማታችን በላይ የወጭ ና የገቢ ንግድ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዝ ታይቶበታል በዚህም የህወሓት ዘረኛ ቡድን በሞኖፖል የያዘው የሀገሪቱ ኢኮኖሚም ከወደቀበት ለማገገም ከቶ አለመቻሉ ከውድቀቱ ወደ ባሰ ውድቀት መግባቱን ያሳያል። ትውልደ ኢትዩጲያውያን በውጭ ሃገራት የሚገኙ ደግሞ ወያኔ እንዳይደርሰው በማድረግ በአማራጭ ዘዴወች ዶላር ለቤተሰብ ወዳጂ መላካቸው ቀጥለዋል። ለዚህም ነው ዛሬም ያች ልማደኛ ህጋዊ ሽፋን ያላት ቀይ ካርድ የተመዘዘችው። በግል ባንኮች የውጭ ምንዛሬ አጠቃላይ ሪፓርት ለብሄራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ ፣በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚገቡትንና ለመሸጋገሪያነት የሚጠቀሙበትን መንገደኞች ይዘውት የሚመጡና ይዘውት የሚወጡ ዶላር ና ጌጣጌጥ እንዲመዘገብ የሚል ህጋዊ ሽፈን ያለው መመሪያ አውጥቷል። በዚህም በጥቁር ገበያ ተመንዝሮ እንዲደርስ የሚደረገውን ለመቆጣጠር እንዲያመቸ መሆኑና ከገባበት የዶላር ጠኔ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ማገገሚያ እንዲሆን ያለመ ነው። ነገር ግን ማሰሪያው ህግ የነሱን አንገት ለመሸምቀቅ አለመቻሉ እንዳሰቡት እንደማይሆንላቸው ከወዲሁ የጥቁር ገበያ ና የባንክ የምንዛሬ ልዩነት እየሰፋ እንደሆነ ታውቋል።በዚህም አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው እየሆነ ይገኛል።

ለወገን መስጨፍጨፊያ ጥይት አይግዙ !!