አባይ ሚዲያ ዜና
አሰግድ ታመነ

በአማርውና በኦሮሞ ህዝቦች ተጀምሮ የነበረው የፍትህና የዲሞክራሲ ጥያቄ መልኩን ቀይሮ የህወሓት አገዛዝ እንዲያበቃ በከፋኝ ሀይሎችና በአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል።

ሁለገብ የሆነ ትግል እያራመዱ ካሉት የነፃነት ሀይሎች በተጨማሪ፣ ለየት ባለ መልኩ በህወሓት ንብረት በሆኑት ድርጅቶች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው ተብሏል።

በዛሬው እለት ብቻ የህወሓት ንብረት በሆኑት በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጃክሮስ በሚባል አካባቢ በሚገኘው እጅግ ግዙፍ በሆነው የወያኔ ኤፈርት ሁሉን አቀፍ አስመጪና ላኪ መጋዘን እና ፋብሪካ በተቀነባበረ ሴራ በተለኮሰ እሳት በትንሹ እስከ 40 ሚሊዎን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተሰል።

በሰሜን ጎንደር ሁመራ ንብረትነቱ የህወሓት የነበረ የተከማቸ 440 ኩንታል ጥጥ መቃጠሉም ተነግሯል።

በተመሳሳይ ቀን በዚ በባህርዳር አመልድ የሚባል የብአዴን ንብረት የሆነ ድርጅት በመቃጠል ላይ መሆኑም ተነግሯል። በዚህም ምክንያት ባካባቢው ከፍተኛ ተኩስና ግርግር መኖሩ ተሰምቷል።

ይህ ጥቃት የነፃነት ሀይሎች በወያኔ ላይ እየወሰዱት ያለ አዲስ ጥቃት ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ተሰጥቶታል።