የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲ ሲ ለጉብኝት እንደተጋበዙ የአሜሪካ መንግስት አሳውቋል

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

አል ሲ ሲ አሜሪካን አገርን የሚጎበኙት በመጪው ኤፕሪል 3 ቀን እንደሚሆን ሁዋይት ሃውስ አስታውቋዋል።

መሪዎቹ የሚጋገሩባቸው ጉዳዮች የስልምና አክራሪነትና የአካባቢው ሰላም እንደሚሆንም የሁዋት ሃውስ ቃል አቀባይ ገልጿል። አይ ሲ ስ የተባለውን የእስላም ሽብረተኛ እንቅስቃሴና አካባቢዊን ማረጋጋት ላይ ያተኩራሉም ተብሏዋል።

የፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ ጉብኝት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሽ ጂንግፒንግ ጋር በፍሎሪዳ ከታቀደው ግንኙነት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ሊሆን ነው ማለት ነው። በዚህ በፍሎሪዳው ስብሰባ ሬክስ ቲልለርሶን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርዶናድ ትራፕ ጋር ይገኛሉ ተብሏዋል።