አዲሱ ሳምሰንግ ጋላክሲ S8 ይፋ ሆኗል!

አዳዲስ የሚባሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መጫኛ አልባ ከጥግ እስከ ጥግ “Infinity display” ትልቅ ስክሪን አራት ስልኩን መክፈቻ መንገዶች (ፓተርን ፓስኮድ፣ የአይን ስካነር እና የፊት ስካነር) ይሄ ማለት የስልኩን ባለቤት ፊት ለይቶ በማወቅ የተቆለፈው ስልክ በራሱ ይከፈታል።

የስልኩ የኋላ ካሜራ ብቃት ያልተቀየረ ሲሆን የፊትለፊት “Selfie” ካሜራው ግን ከበፊቱ የጋላክሲ S7 ተሻሽሎ 8MP ሆኖ መጥቷል።

ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መልኩ ልክ እንደ አይፎን ሁሉ አዲሱ ጋላክሲ S8 እና S8 Plus ተብሎ በሁለት መጠን ቀርቧል። ይሄ ምናልባትም ባለፈው አመት በNote 7 ላይ ከደረሰው ውድቀት የተነሳ ሳምሰንግ ያንን ትልቅ መጠን ያለው ሞዴል እስከወዲያኛው ገድሎ ጋላክሲን በሁለት መጠን ለማቅረብ ወስኖ ይሆን? የሚል ግምት አለኝ።

ከሶስት ሳምንት በኋላ ለሽያጭ የሚቀርበው ጋላክሲ የS8 ሞዴሉ 720 ዶላር እንዲሁም የS8 Plus ሞዴሉ ደግሞ 820 ዶላር በማውጣት በስማርትፎን ታሪክ ይህ ስልክ እጅግ ውዱ ስልክ ይሆናል።

The new Samsung Galaxy S8 is unveiled!

So what are some of the new features: Infinity display with a curved edge and button-free screen to maximize the display size. So, that means, instead of a physical home button, there is not a virtual on-the-screen button. Four ways to unlock the phone – the traditional pattern or passcode, finger scanner at the back of the phone, retina scan, and face recognition.

Back camera quality is the same as S7, but the front facing “selfie” camera got improved to 8MP.

In my opinion, the fact that the new Galaxy comes in two sizes, S8 and S8 Plus, is an indication to recoup from the Galaxy Note 7 disaster and may be killing that model forever.

Starting at $720 for the Galaxy S8 and $820 for the Galaxy S8 Plus, this will be the most expensive smartphone ever! Galaxy S8 and S8 Plus will be available for purchase in the US on April 21.