የሱዳኑ መሪ ኦማር አል በሺር የዮርዳኖስ ጉብኝት ተቃዉሞ ገጠመው

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

በተባባሩት መንግስታት የሰባዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛይድ ራ አ ድ አል ሁሴን በዚህ ሳምንት የሱዳኑን መሪ የኦማር አል በሺርን የዮርዳኖስ ጉብኝት ተቃወሙ።

ተቃውሞው አል በሺር ወደ አረብ ማህበር ስብሰባ እንዳይመጡ፤የዓለም አቀፍ ፍረድ ቤት፡ “ባለበት፤ በሄደበት ተይዞ ለፍርድ ይቅረብ” የሚለውን ውሳኔ ዮርዳኖስም ተፈጻሚ ማድረግ ይገባታልም የሚል ነው። ዮርድኖስም የዓለም አቀፍ የሰባዊ መብት ፍርድ ቤት አንዷ ፈራሚ አባል በመሆኗም ነው ኦማር አል በሺርን በፍርድ እንድታግት የተጠየቀው።ኦማር አል በሺርን አላግትም ማለት የዓለም አቀፍ ፍረድ ቤትን ውሳኔ መጣስ መሆኑ ነው።

አል በሺር በዳርፉር ጭፍጨፋ ተጠያቂ ናቸው ከተባለ ቆይቷል።በአገራቸው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከወያኔ መንግስት ጋር በመቧደን እንደሚያስሩና ለወያኔ እንደሚሰጡም የሚታወቅ ነው።