ኢትዮጵያ ውስጥ በረሀብ ከ 5.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል Caritas የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ገለጸ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
በናትናኤል መኮንን

ኢትዮጵያ ውስጥ በረሀብ ከ 5.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ልጆች ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የሞት አደጋ ውስጥ እንደሆኑ Caritas የተባለው  የበጎ አድራጎት ድርጅት አሳወቀ።

በስዊዘርላድ ለስደተኞች ምግብ የአልባሳትና የገንዘብ እርዳታ የሚለግሰው Caritas የተባለው ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፍልጋቸው ሃገሮች በስዊዝ የሚኖሩ ዜጎቹንና ድርጅቶችን የገንዘብ እርዳታ ጠየቀ።

ከነዚህ ሃገር ውስጥ በቀዳሚነት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከሚይስፈልጎት ውስጥ ኢትዮጵያ 5.6 ሚሊዮን ሰዎች በመራባቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይዛልች።

Caritas የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ድርጅት አክሎ እደተናገረው በኢትዮጵያ ከእህል እርዳታው በተጨማሪ የውሃ መስኖዎች እንደሚሰራና የእህል ማዳበሪያዎችን እንደሚለግስ አሳውቋል።

በተጨማሪም በየትምህርት ቤቱ በምግብ እጥረት ለሚሰቃዮት ልጆችም ተጨማሪ እርዳታዎችና በቦታው ላይ ህክምናንና ትምህርትን እንደሚሰጥ ካሪታስ የተባለው ድርጅት  ገልጿል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ እርዳታውን የሚጀምርባቸው በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች እንደሚሆን ለመረዳት ተችሏል።

በተጨማሪም ድርጅቱን በገንዘብ ለሚረዱ Caritas Schweiz በማለት 60-7000-4, የሚል የባንክ ቁጥር አስቀምጥዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ከስር ያለውን ሊንክ ይክፈቱና ይመልከቱ