ፕሮፓጋንዳው ይህንን ያህል አይን አውጥቷል (Video)

አባይ ሚዲያ ዜና
ዳዊት እያዩ

አራት ኪሎ ጀርባ ያሉ ቤቶች መብራት አጥተው እየተሰቃዩ በሚነገርበት ወቅት የመንግስት ሚዲያ የሆነው ኢቢሲ ሕዝቡን ለመደለል አንድ ዶክመንተሪ እንዳቀረበ ታውቋል

ዚሁ ዶክመንተሪ ደቡብ አፍሪካም ከኢትዮጵያ የኤሌትሪክ ሃይል ለማግኘት እየተጠባበቀች መሆናን በሚያስገርም ሁኔታ ተነግሯል

ግብጽን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አገራትም በየመን ኩል በሚዘረጋ የኤሌትሪክ ማስተላለፊያ ሃይል እንደሚደርሳቸውም ተገልጿል።

የመብራት ኃይል ሥራ አስኪያአውሮፓም እኛን እየጠበቀ ነው በእዛ በኩልም ኮሪደር አለ በማለት የሰጡት ገለጻ በብዞዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህን ዶክመንተሪ ተከትሎ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ብዞዎች አስተያየታቸውን እያሰፈሩ ይገኛሉ።

ከነዚህ አስተያየቶች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል።  “እንዴ! ትንሽ ማፈርም የለም እንዴ? አውሮፓ መብራት ካስገባ ስንት ዓመቱ ነው? መብራት እንደ ሽቦ አልባ ስልክ ገመድ አልባ ነው እንዴ?”

ባለፈው ቅዳሜ የመንግስት ሚዲያ በሆነው ኢቢሲ የተላለፈውን ይህን ዶክመንተሪ ቪዲዮ በተጨማሪ እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል።