በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ሱቆች በነጋዴ አድማ ተዘግተዋል

0

አባይ ሚዲያ

ጋሻው ገብሬ

የላይቤሪያ ብሄራዊ ፖሊስ ዝግጁ ሆኖ ቢወጣም በዋና ከተማው የአገር ወዳድ ነጋዴዎች ማህበር ሱቆች ሁሉ በአድማ አንዲዘጉ አዝዋል ሲል ኦል አፍሪካ ዘግቧል።

ትላንት ሰኞ ማለዳ አንስቶ ዋተር ሳይድ ከተባለው የዋና ከተማው ትልቅ ገበያ ሱቆች ተዘግተው ውለዋል።የነጋዴ ማህበሩ ባለፈው ፌብሩዋሪ ተመመሳሳይ የሶስት ቀን አድማ ጠርቶ እንደ ነበር ኦል አፍሪካ ዘግቧል።

ኦል አፍሪካ እንዳለው የነጋዴ ማህበሩ ቅሬታውን ለፓርላማ አቅርቦ ነበር።ከመንግስት የቀረበው ማስፈራሪያ ብቻ ነው።መንግስት የሚለው ነጋዴዎች ተገደው በማስፈራሪያ አድማውን ተቀላቅለዋል ነው።የመንግስቱ ተጨማሪ መግለጫ የሚለው አድማው ኢኮኖሚውን ይጎዳል ነው።የአድማውን መነሻ ምክንያት ወይም የነጋዴውን ብሶት አያብራራም።

አካባቢውን የቃኘው የኦል አፍሪካ ዘጋቢ በሞንሮቪያ ሱቆች ማለዳ ይከፈቱና ንግድ የጀመራል።የሰኞው ሁኔታ ግን በጣም ልዩ ነው።ሱቆች ዝግ ሆነው፤የፖሊሶች መኪናዎች መንገዱን ሞልተው የአደጋ ድምጽ አንያምባረቁ ይዞራሉ ብሏዋል።