ከ2000 በላይ ስደተኞች ሜዲትራንያ ባህር ከመስመጥ ድነዋል

አባይ ሚዲያ

ጋሻው ገብሬ

ስደተኞቹ በአስገራሚ ሁኔታ ህይወታቸው የዳነው ዛሬ አርብ እለት መሆኑን ቪ ኦ ኤ ዘግቧዋል።

የጣሊያን የባህር ጠረፍ ጠባቂ 19 ነፍስ አድን እንቅስቅሴዎች በጠረፍ ጠባቂዎችና፤የመንግስት ያልሆኑ መርከቦች ተካሂደው በጠቅላላው የ2074 ስደተኖችን ንፍስ አትርፈዋል። ስደተኖቹ ይጓዙ የነበሩት በ 16 የላስቲክ ና ሶስት ትናንሽ የእንጨት ጀልባዎች ነበር።

ለስደተኞች የህክምና እርዳታ በማድረግ የሚታወቀው ሜዲሲን ሳን ፍሮንቲየ የተሰኘ ድርጅት አንድ ልጅ ብቻ አንደኛው የላስቲክ ጀልባ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል ብሏዋል።ይሄው ግብረሰናይ “ባህሩ መቃብር መሆኑ ቀጥሏል” ይላል በሶሻል ሚዲያ ባስተላለፈው መልክት።

ሰደተኞቹ ወደ ኢጣሊያ ወደቦች ይወሰዳሉ ብሏዋል ሜዲሲን ሳን ፍሮንቲየ።

የዓላም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት በዚህ ዓመት ብቻ 32,000 ስደተኞች በባህር ተጉዘው ወደ አውሮፓ መጥተዋል።ከዚህ መሃል 650 ሞተዋል ወይም የደረሱበት አይታወቅም።