ባለፉት ጥቂት ወራቶች አንድ ቻይናዊ ቢሊዮኔር የአንድን ትልቅ የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣን ሙስናን ይፋ ስለአወጣ አሁን ተፈላጊ ወንጀለኛ ሆነ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ባለፈው እሮብ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ቻይናዊው ቢሊዮኔር ጉዎ ወንጉይ እንተርፖል(የአለም ፓሊስ ድርጅት) አድኖ እንዲይዘው ጠይቋዋል። ይህ የሆነው ጉዎ ወንጉይ በቴሌቪዥን  ቀርቦ ሙስናን የሚያጋለጥ ”የኑክሌር ቦምብ” ብሎ ያለውን ጉድ ከመዘርገፉ በፊት ነው። ጣት የተጠቆመበት ባላስልጣን የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባል ነው።

ቢሊዮኔር ጉዎ ወንጉይ የአምሳ ዓመት እድሜ ያለው ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ከቻይና ውጭ መኖር ተገዶ ቆቷል። ባለፈው ማርች ወር አንድን የከፍተኛ የኮሙኒስት ፓርቲ በለስልጣን ልጅ በሙስና ከሰሰ። በኤፕሪል ወር ኒው ዮርክ ታምስ የተባለው ጋዜጣ ይህኑ አረጋገጠ። ቻይና ይህኔ ነው ለኢንተርፖል መልዕክት የሰደደችው።

ቻይና የፈለገችው ኢንተርፖል ለአባላት አገሮች በሙሉ ማዘዣ እንዲልክ ይህም በይፋ መልክት የተነገረው በቻይና የውጭ ጉጋይ ሚኒስትር ቤጂንግ ላይ እሮብ በሰጠው ማግለጫ ነው። ማዘዣው ኢንተርፖል ቀይ ምልከት የተሰኝው ሲሆን ሁሉም አገራት ይህን ማዘዣ የግድ ተፈጥጻሚ የሚያደርጉት አይደለም።

ጉዎ ወንጉይ እንደሚለው ሁሌ ከአማሪካ ወንጀል መርመራ ክፍል ጋር እገናኛለሁ ምንም እያዛለሁ የሚል ስጋት የለኝም ብሏዋል።

ቱጃሩ ጉዎ ወንጉይ አገሩ ቻይና የምትከሰው 8.7 ሚሊዮን ዶልላር ለአንድ ማ ጂያን የተባለ የቻይና ከፍተኛ የጸጥታ ክፍል ባላስልጣን በጉቦ መልክ ገንዘብ ሰጥቷዋል ብላነው። ማ ጂያን የጉዎ ጠባቂ ወድጅ ተብሎ በቻይና ጋዜጦች ይፋ ወጥቶበታል። ጉዎ ወንጉይ ይህን ይክዳል። ኢንተርፖል ቢፈልገውም እሱ ዛሬ ያለው ማንሃታን ኒውዮርክ ነው። የማር አላጎ መዝናኛ የተባለው የዶናልድ ትራምፕ መዝናኛ ክበብም አባል ነው።

ጉዎ ወንጉይን ሁለት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኖች በመኖሪያው ተገኝተው ቃለ መጠይቅ አድርገውለታል። የማንሃታን መኖሪያ አፓርተማው በ $67.5 ዶላር የገዛው ነው። ቃለ መጠይቁ አንዳይካሄድ የቻይና በለስልጣኖች ቪኦኤን ጠይቀው ነበር።ዘረግፈዋለሁ ያለው ነገር ሳይወጣ ቃለ መጠይቁ ሲካሄድ ሁለተኛው ሰዓት ላይ በድገት እንዲቋረጥ ሆንዋል። ቻይና የምትለው ይህ የአገር ውስጥ ጉዳይ ነውና ጣልቃ ገብነት ተደረገብኝ ነው።

ቢ ኦ ኤ ነጻ የተሰኘ በአሜሪካ መንግስት ድጋፍ የሚንቀሳቃስ ተቋም ነው። ራዲዮ ጣቢያው የሚለው ቃለ መጠይቁ የተቋረጠው ከተፈቀደላት ሰዓት በመዝለሉ ነው። የተቀረው የቃለ መጠይቁ ክፍል ተቀድቶ ጥያቄ ለሚኖራቸው ጋዜጠኞች ይቀርባል ብሏል። ማንም ባላስልጣን ቃለመጠይቁን አቋረጡ ብሎ አልጠየቀንም ብሏል ቪ ኦ ኤ።