የኬንያ ጦር ሃይል የአልሸባብን 52 ታጣቂዎች ገደለ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ግብሬ

የኬንያ መከላከያ ጦር ሃይል ዛሬ የሰጠው መግላጫ ጠቅሶ ሬውተር የዜና ወኪል እንደዘገበው የአልሸባብ 52 ተዋጊዎችን የኬንያ ጦር ሃይል መግደሉን አሳውቋል።

ዛሬ አርብ ዕለት በደቡብ ሶማሊያ በሚገኘው የአል ሸባብ ካምፕ ላይ የኬንያ ሃይሎች ጥቃት አድርሰው አንደነበር ኮሎኔል ዮሴፍ ኦዉት የኬንያ ጦር ሃይል ቃለ አቀባይ ገልጿል። ጥቃቱ የተፈጸመው ባርዴሬ ከተባለ ስፍራ ታች ጁባ ክፍል ነው።

በካምፑ ውስጥ ጠመንጃዎች በፈንጂነት ሊሰሩ የሚችሉ ቁሶችና የቦምብ መስሪያ ቁሳቁሶችም ተገኝተዋል።

ጥቃቱ ሊፈጸም የቻለው አሰሳ ሲደረግ አል ሸባቦች ታጣቂዎች ተከማችተው ያሉበት ቦታ ሲደረስበት ነው። በምድር ያለው ሰራዊት በመድፍ በመጠቀም ካምፑን መደምሰስ ችሏዋል ይላል መግላጫው። ከአል ሸባብ 52 ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ሌሎች ቆስለው እንደሸሹም ማግላጫው አትቷል።

ኬንያ በሺ የሚቆጠር ሠራዊት በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስጠባቂ በተሰኝው ሠራዊት ውስጥ አሰልፋለች። ይህን ያደረገችው መጀመሪያ በአሸባሪዎች ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ነው።

አል ሸባብ የአል ቃይዳ ወገንና የራሱን ጭካኔ የተሞላ የስልምና ዘርፍ የሶማሊያ ህዝብ ላይ እጭናለሁ ብሎ የሚዋጋ አሸባሪ ሃይል ነው።