የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገር ጸጥታ ምክር ቤት አማካሪ ለነበሩት ጄኔራል ፍሊን የአሜሪካ መከላከያ ፔንታጎን ማስጠንቀቂያ ሰጠ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የቻይና ዜና ምንጭ ሰበር ዜና ብሎ ዛሬ እንደገለጸው ጄኔራል ፍሊን አዲስ ምርመራ ተከፍቶባቸዋል ሲል ሲ ኤን ኤን የተባለው አለም አቀፍ ዜና ድርጅት ገለጠ፤ በማከልም ጄኔራሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብሏል።

ጄኔራል ፍሊን ስራቸውን እንዲለቁ ከተደረጉ ቆይቷል። ለክስም ያበቃቸው የአሜሪካ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ሩሲያ በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ እጅዋን እንድታስገባ ማሳሪያ ሆነዋል በሚል ክስ ነው። ሩሲያ መርጫውን ወደ ምትፈልገው አቅጣጫ አዙራዋለች የተባለው ሃሳብ በሰፊው እየተነገረ ነው።

በጊዜው ጄኔራል ፍሊን የፕሬዚዳንት ትራምፕ ምክትል ለሆኑት ማይክ ፔንስ ስህተት የሆነ መረጃ ሰጥተዋል በሚል ተከሰዋል። የክሱ ጭብጥ ጄኔራል ፍሊን ከሩሲያው አምባሳደር ሴርጌ ኪስልያክ ጋር ያደረጉትን የንግግር ፍሬ ነገር አለመግለጻቸው ነው።

በአሜሪካ ምክር ቤት እውቅ የሆኑት የዴሞክራቶች ፓርቲ አቢይ አባል ኤላይጃ ካሚንግስ “ጄኔራል ፍሊን ከውጭ አገር ምንጮች የተቀበሉትን ገንዘብ ለምን የመከላከያ ሚኒስቴር እያስጠነቀቃቸው ደብቀው ተገኙ የሚለው አሳሳቢ ነው” ብለዋል።

ኤላይጃ ካሚንግስ በተጨማሪ “ለምን ኋይት ሃውስ ይህን እንደሚደባብቀው አይገባኝም” ብለዋል።