የሶማሊያ ከፍተኛ ሚኒስትር በመንግስት ጸጥታ ሃይል ተገደለ

አባይ ሚዲያ ዜና
በዘርይሁን ሹመቴ

የ31 አመቱ የሶማሊያ ሚኒስቴር የሆነው አብዱላሂ ሸኪ አባስ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደሉ ተሰማ።

የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች የ31 አመት ወጣት ሚኒስቴሩን አሳፍሮ ሲሽከረከር በነበር መኪና ላይ በከፈቱት ተኩስ ሚኒስትሩ ሊገደል እንደቻለ ተነግሯል።

የጸጥታ ሃይሎቹ ሚኒስትሩን በጫነው ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ የከፈቱት የአሸባሪ መኪና ይሆናል በማለት በወሰዱት የተሳሳተ ግምት መሆኑንም ታውቋል።

በሚንስትሩ ግድያ ምክንያት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ስብሰባ ሲያካሄዱበት ከነበረው ኢትዮጵያ ወደ ሶማሊያ እንደገቡ ተነግሯል።

አብዱላሂ ሸኪ አባስ የሚንስትርነት ደረጃ ላያ ከመድረሳቸው በፊት በስደተኛ ካምፕ ውስጥ አስቸጋሪ የህይወት ጎዳና እንዳለፈ ታሪኩ ይናገራል።

ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ በሚንስቴሩ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ ይህን አሳዛኝ ገጠመኝ በጥልቀት እንዲመረመር ትእዛዝ መስጠታቸውም ታውቋል።