የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጻሀፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ድርቅ ለተመታችው ሶማሊያ $900 ሚሊዮን ጠየቁ

አባይ ሚዲያ
ጋሻው ገብሬ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጻሀፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሶማሊያ የወደፊት እድል በእንጥልጥል ላይ ነው ብለዋል። ባንድ ወገን ረሃብ በሌላ ወገን በጽንፈኞች ሽብር ሲሉ ተናገረዋል። በዚሁ ንግግራቸው በድርቅ ለተመታችው ሶማሊያ $900 ሚሊዮን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ዛሬ ዜናውን ያቀረበው ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ “እንዲህ ያለ ድርቅ፤እንዲህ ያለ የበሽታ አይተን አናውቅም” ማለታቸውን ግልጿል። በሶማሊያ እጅግ በጣም የተጠቃው የአገሪቱ ክፍል በእስላማዊ ታጣቂ አል ሸባብ የተያዘው ነው።

ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግራቸውን ያሰሙት ስለሶማሊያ ጉዳይ ሎንዶን ላይ በተዘጋጀ ስብሰባ ነው። በ2011ዓም ረሃብ 250,000 ሰዎችን በሶማሊያ ገድሏል።

በዚሁ ስብሰባ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ የሶማሊያን ጸጥታ ሀይል ለማጠናከርና ዛሬ በረሃብ ለሚጠቃው 6 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታውን ለማፍጠን ቃል ገብቷል። ቴሬሳ ሜይ ዓላማችን “የሶማሊያ መንግስት ሀይሎች አል ሸባብን አዳክመው የበላይነት እንዲያገኙ ነው” ብለዋል።

ስለሶማሊያ ጉዳይ ሎንዶን በተጠራው ስብሰባ የአፍሪካ መሪዎችም ተገኝተው ነበር። መሪዎቹ የመከሩት ሶማሊያ እንዴት የዓለማቀፍ እረዳታ እንደምታገኝ ጸጥታ ሀይሏም ስልጠና አግኝቶ ጠንክሮ 2020 እንዴት በሶማሊይያ ዴሞክራሲያዊ መርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ነው።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ “ፎርማጆ” ሲናገሩ “አል ሸባብ በሁለት ዓመታት ይሸነፋል። የሶማሊያን ብዙ አገራት ግን ብድርዋን መሰረዝ ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስትና የአፍሪካ ህብረት አል ሸባብን ጠራርጎ ለማውጣት ላለፉት አስር ዓመታት ታግለዋል። አሸባሪው ቡድን ግን በዚህ ሳምንት እንኳ ስድስት ሰዎች የሞቱበት አጥፍቶ የመጥፋት የቦምብ አደጋ አድርሶ ስድስት ሰዎች በዋና ከተማዋ ሞቅዲሾ ሞተዋል።

የመንግስታቱ ዓላማ 20,000 ሰው ብርታት ያለው የሶማሊያ ጸጥታ ሃይል የጸታውን ሃላፊነትን ከአፍሪካ ህብረት ላይ በ2020 ዓም እንዲረከብ ነው።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ግን ይህ የሚሆን አይመስለኝም። የጸጥታ ሃይሌን ከሶማሊያ የማወጣው ድንበሬ ሲከበር አል ሸባብም ሲወድም ነው በማለት ተናግረዋል። “በችኮላ ለመውጣት እንችልላለን ግን የሶማሊያ ሃይሎች ሳይጠነክሩ እንዳሻቸው ብለን ብንሄድ ችግሩ የሶማሊ አይደለም የኛ ነው” በማለት ጨምረው ተናግረዋል።

በ2012 ኬንያ 4,000 ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት በኩል አሰልፋለች።

አፍሪካ ህብረት( AU’s Amisom) ከቡሩንዲ፤ጂቡቲ፤ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ኡጋንዳ 22,000 ጦር በሶማሊያ አሰልፏል።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሶን የሶማሊያ መሪዎች ስለ ጸጥታ ምን አንዳቀዱ የጦር ሀይል ለመገንባት ያላቸውን እቅድ ያውጡና ያቅርቡ። በምላሹ ከዓለም አቀፉ ህብረተሰብ እርድታውና ስለጠናው ይቀርባል። ሁኔታዎች ሲያመቹ ደግሞ የሶማሊያ ሀይሎች ከተባበሩት መንግስታት ጸጥታ ሃሎች የሶማሊያን ጸጥታ ጉዳይ ይረከባሉ ብለው ተናግረዋል።