በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት ተጠርጥረው ከአንድ ቤተሰብ 3 ወንድሞችና እህቶች ታስረዋል!

0

በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት ተጠርጥረው ከአንድ ቤተሰብ 3 ወንድሞችና እህቶች ታስረዋል፣አንድ ወንድማቸው በትግል ወቅት ተሰውቷል፣የ73 ዓመት አዛውንት አባታቸው የመከላከያ ምስክር ሆነው ቀርበዋል።

እነ ሉሉ መሰለ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ!!!

(በሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው እንዲከላገሉ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲከላከሉ የተበየነባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ የአርባ ምንጭ የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ አቶ ሉሉ መሰለን ጨምሮ 7 ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ፡፡

አቶ ሉሉ መሰለ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካል በሚል ለቀረበበት ክስ በመከላከያ ምስክርነት የቀረበው ጌታሁን በየነ እና ሌሎች ከኤርትራ መጡ የተባሉና በቂሊንጦ በእስር ላይ የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል እነደሆኑና በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ኤርትራ እነደሄዱ ሉሉ እንዳልመለመላቸው ተናግረዋል፡፡

ሌላዋ ተከሳሽ አየለች አበበም የመከላከያ ምስክሮቿን አቅርባ አሰምታለች፡፡ ምስክሮቹም መምህር እንደሆነችና በመኖሪያ ቤቷ ተገኘ የተባለው መሳሪያ ውሸት እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ በምስክርነት የቀረበውና በእስር ላይ የሚገኘው ወንድሟ ወንዶሰን አበበ ሰላም እንድላት ይፈቀድልኝ እምባ እየተናነቀው የጠየቀውና ተፈቅዶለት ከእህቱ ጋር ሲገኛኑ የነበራቸው ሁኔታ በችሎት የነበረውን ታዳሚ ልብ የነካና በእንባ ያራጨ ክስተት ነበር፡፡

የአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ አቶ በፍቃዱ አበበ ሰባት አመት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ወንዶሰን አበበ በቂሊንጦ አየለች አበበ በቃሊቲ እስር ቤት በግፍ እስር ላይ ትገኛለች፡፡ ወንድማቸው አቶ እንግዳ አበበ አርባ ምንጭ አካባቢ ከአገዛዙ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ እንደተሰዋ ተገልጥዋል፡፡