በምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ ጎጆ 01 ቀበሌ በሕዝባዊ አመፅ ስትናጥ ዋለች

0

ግንቦት 04/2009 በምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ ጎጆ 01 ቀበሌ በሕዝባዊ አመፅ እየተናጠች መዋሏንና ማምሻውን ደግሞ የቀበሌው ወጣቶች ጎዳና ላይ አሮጌ ጎማዎችን በማቃጠልና መንገድ ለመዝጋት  ድንጋይ በመደርደር ተግባር ተጠምደው ማምሸታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ህወሃትንና አባል ድርጅቶቹን በመፈክር ሲያወግዝ እንደዋለ በተነገረው የምዕራብ  ሸዋ ጀልዱ ከተማ ተቃውሞ ወጣቶች ለሥራ ፈጠራ የታደላቸው ገንዘብ በኢሬቻ በዓል ላይ ለተገደሉ ወንድሞቻቸው የደም ካሳ ሊሆን እንደማይችል በመፈክር ድምጻቸውን ማሰማታቸው ተስተውሎበታል ተብሏል። ከመንገድ መዝጋትና ጎማዎች ማቃጠል በተጨማሪ ቀደም ሲል በደርግ ጊዜ የጎልማሶች  ማሰልጠኛ ሆኖ ያገለገለና ወደ  ጀልዱ የቴክኒክ ሞያ ት/ቤትነት  ከተቀየረ በኋላ በህወሃት ትእዛዝ ወታደራዊ ካምፕ በሆኑ ህንጻዎች ውስጥ የነበሩ ኮፒዩተሮች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውና በቤቶቹ ውስጥ የነበሩ ፍራሾች እንዲቃጠሉ መደረጋቸው ታውቋል።