የመጨረሻዎቹ የእምዬ ዳግማዊ ምኒሊክ ቤተሰቦች

ዳግማዊ አፄ ምንይልክ ከአባታቸው ከንጉስ ኃ/መለኮት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ እጅጋየው ለማ አድያሞ በነሐሴ 12 1836 ዓ.ም በአንጎለላ ከተማ ልዩ ስሙ እንቁላል ኮሶ በተባለው ቀዬ ተወለዱ እንዴት ተወለዱ የሚለውንና የመጨረሻው ቤተሰብ የሚባሉት እንደሚከተለው እናያለን፦
1ኛ. ቸኮል ለማ አድያሞ
2ኛ. ፍልፍሉ ለማ አድያሞ
የወ/ሮ እጅጋየው አድያሞ ወንድሞች በአንጎለላ የንጉስ ሳህለ ስላሴ ወታደር ሆነው ሲያገለግሉ አካባቢው ላይ በተፈጠሩ ችግሮች ሁለቱም በተለያየ ቀናት ይሞታሉ በዚህ መሪር ሃዘን የወንድሞቻቸውን ሞት ውሎ ለመዋል (እርም ለማውጣት) ከመንዝ ቀዬቸው ይመጣሉ በዚያን ግዜ ወ/ሮ እጅጋየው ከቤተሰቡ በጣም ልጅ ስለነበሩ እና ሃዘንና መንገድ ተጨምሮ ይደክማሉ በቤተ መንግስቱ ለሃዘኑ ከቤተሰባቸው ጋር ከሰነበቱ በኃላ ሊመለሱ ሲዘጋጁ የንጉሱ ባለቤት ወ/ሮ በዛብሽ የእጅጋየውን ደርባባነት መልካምነት ካዩ በኃላ ቤተ/መ ውስጥ እንዲቀሩና ልጆች እንዲንከባከቡ ንጉሱን አስፈቅደው አንጎለላ እንቁላል ኮሶ ከተቀመጡ በኃላ እጅጋየው ወደ አንኮበር ቤተመንግስ እንዲሄዱ ተደረገ
ወ/ሮ በዛብሽ ለልጃቸው ለሰይፈ ሹክ አሉት እሱም እጮኛ ስለነበረው በለሆሳስ እሺ ብለው ለወንድሙ ለኃይለ መለኮት ይሉና አሳመኗቸው ጊዜ ጠብቀው አንድ ለሊት እንዲህ ሆነ ወ/ሮ እጅጋየው ከማህፀናቸው ፀሃይ ሲወጣ በህልም ያያሉ ነገሩንም ለባልደረቦቻቸው ይናገራሉ ሆኖም እዚህ ግቢ ያላቸው አልነበረም።

ከቀን ወደቀን ንጉሱ ሰሙ ነገሩን ችላ ባለማለት ምንድነው እያሉ ባለበት ሁኔታ ኃ/መለኮት እጅጋየው ጋር ደረሱ እያደር እርግዝናው ገፋ የንጉሱ ባለቤት ሰይፈን ቢጠይቁት ከኔ አደለም አሉ ከዚህ በኃላ እጅጋየው እጅና እግራቸው በእግር ብረት ታስሮ በአንድ ክፍል አስቀመጧቸው ወ/ሮ በዛብሽ ኃ/መለኮትን ጠይቀው ሲያረጋግጡ ከእስረሸ አስፈቷቸውየልጁ መወለድ ይጠበቅ ጀመር ቀናቸው ሲደርስ የንጉሱ ታማኝ ወታደሮች ወዳሉበት እንቁላል ኮሶ በ1836 ዓ.ም ወሰዷቸው ንጉሱ ወደተወለዱበት ሸዋ ሮቢት ለስራ ለመሄድ ተነሱ
እንዲህ አሉ ይህች ልጅ በደረሰች (ምጧ በመጣ) ጊዜ ፈጥናቹ አሳውቁኝ ብለው ሄዱ መጣው መጣው ሲል ፈጣን መልክተኛ ሄዶ በአራት ሰንጋ ፈረስ እያቀያየሩ ሲደርሱ ፀሀዩ ሲወለዱ እኩል ንጉሱም ለልጅ ልጃቸው ምንይልክ ሸዋ ብለው ሰየሙት እንቁላል ኮሶ ተወልደው አንጎለላ ኪዳነምህረት ክርስትና ተነስተው ለ ሶስት አመት አፈር ፈጭተው አቡክተው ካደጉ በኃላ እናታቸው ለትምህርት ወደ መንዝ ወሰዳቸው
አንጎለላ የቀሩት የወ/ሮ እጅጋየው ታላቅ ወንድም የአብስራ አድያሞ ትዳር ይዘው ስለነበር አቶ አየሁባይኔን ወለዱ አቶ አየሁባይኔ ደግሞ ወ/ሮ አንቺንአሉን ወለዱ ወ/ሮ አንቺንአሉ ደግሞ አቶ ገ/ማርያም ገ/ፃድቅን ወለዱ አቶ ገብረ ማርያም የመጨረሻ ልጅ ስለነበሩ ከንጉስ ሳህለስላሴ ግዜ ጀምሮ የነበረውን ቦታ ይዘው ትዳር መስርተው እምዬ የተወለዱበት አባታቸው እሳቸው የተወለዱባት መሬት ላይ ሰባት ልጆችን ወለዱ በመጨረሻም ሶስት መንታ ልጆች ተወለዱ።

እናም እድላቸው ገጥሞ ሊቀ ሊቃውንት ነሲቡ የታእካ ነገስት ባእታ ለማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ዳግማዊ ምኒልክ የተወለዱበትን ቦታ ለማየት እና መታሰቢያ ለመስራት ሲመጡ ሱስቱንም በመመልከት አ.አ እንዲሄዱ ተደረገ ቦታው እንደገና ከተረሳ በኃላ አቶ ኃይለ መስቀል የተባሉ ልጆቹን እንደ አባት ይንከባከቡ የነበሩ ወደ ታእካ ነገስት ባእታ ለማርያም ገዳም አ.አ ከደብረብርሃን ይደውሉና የሶስቱን ለጆች ደህንነት ከጠየቁ በኃላ የእምዬ ቤተሰብ መሆናቸውንና የተወለዱበት ቦታም ምንም መታሰቢያ አለመኖሩን ለቦርድ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ሀ/ጎርጊስ ከሀብትይመር ካወያዩዋቸው በኃላ ሶስቱም ትምህርት እረፍት ሲሆኑ ሀ/ጎርጊስ ከሀብትይመር ታሪካዊ ቦታውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማገናኘት ይዘዋቸው ሄዱ በቦታው ታሪካዊነት በመደመም ለእምዬ መታሰቢያ ቦርዱ አንድ መታሰቢያ መሰራት እንዳለበት አ.አ ሲመለሱ ለቦርዱ አሳምነው ፈቃድ አገኙ በ1978 ዓ .ም በ78 ሺህ ብር መታሰቢያ ክሊኒኩ ተሰርቶ ለጤና/ጥ/ሚ የታእካ ነገስት በኣታ ለማርያም የዳግማዊ ምኒልክ ባለ አደራ ቦርድ አስረከበ።

ክሊኒኩ በማንም የመንግስ አካል አደለም የተሰራው እንደሚታወቀ ከአስር አመት በፊት ባላታወቀ መልኩ ቢዘጋም አሁን በታሪክ አስከባሪ ትውልዶች አማካኝነት ተከፍቶዋል:: ንግስት ዘውዲቱ የአባቴን ማስታወሻ አደራ ብለው የሰጡት የታእካ/ነ/ባ/ ለማርያም የቦርድ ሰብሳቢ ደጃዝማች ከበደ ተሠማ ናቸው አደራቸውንም ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት አርገዋል ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን ቦታው ላይ በ1965ዓ.ም በመውሰድና ታሪኩንም በማሳወቅ በሃላም ቦርዱን አሳምነው ሃላፊነቱን ለሃ/ጎርጊስ መሃንዲስም ስለነበሩ ለሳቸው ሃላፊነቱንም ሰተዋል ሃይለ ጎርጊስም በደንብ ተወተውታል እነዛ ሶስት መንታ ልጆች አንዱ በእስራኤል ይኖራል አሰበፃዲቅ ገ/ማርያም ይባላል ሁለተኛው ሀይለማርቆስ ገ/ማርያም የጉዞ አድዋ ሦስት አዲስ መንገድ በመቀየስ እዛው በመውሰድና የገብርዬን አፅም አይተው አብሮ ተሳታፊ በመሆን አ.አ ይገኛል
ሶስተኛዋም እዚሁ ትገኛለች ሚስጥረ ገ/ማርያም ታላቅ ወንድማቸው አቶ ወርቅ አገኘሁ ገ/ምርያም እዛው እምዬ ከተወለዱበት 100 ሜ.ር እራቅ ብለው የአካባቢውን ታሪክ በማስጠበቅ ሲገኙ  የሳቸው ታናሽ አቶ ሀብቴ ገ/ማርያም በአቅማቸው በአመት የቻሉትን ያህል ሰው በመውሰድ ወንድማማቾች ተሰብስበው የድሮውን መስተንግዶ በማረግ ያስጎበኛሉ::

ዘንድሮ በቀረበልኝ ጥሪ መሰረት እኔም ከነያሬድ ሹመቴ ጋር ተካፋይ ነበርኩ እጅግ በጣም መግለፅ በማልችለው ደስታ ተመልሰናል በየአመቱ ሚያዚያ 30 የሄደ ዮሃንስን አንግሶ ታሪክና ባህልን ተመግቦ ይመለሳል የዚህን ታሪክ ከሶስት አመት በፊት አቶ ሀብቴ ገ/ማርያም ከጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ ጋር በአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ቃለመጠይቅ አድርገዋል ተጨማሪ መረጃ ከደጃዝማች ከበደ ተሠማ ልጅ አስፋው ከበደ ማግኘት ይቻላል የህፃናቶቹ ፎቶ ባእታ ነገስት ለማርያም ገዳም ካሳተመችው መፅሃፍ የተወሰደ ነው ሌላው የሃይለማርቆስ እና አቶ ሀብቴ ገ/ማርያም ናቸው::-