ብአዴን በህወሀት ደጋፊና ተቃዋሚ ለሁለት መከፈሉ ተነገረ

0

ሕወሃትን በሚደግፉና በማይደግፉ የብአዴን አመራሮች መካከል ከፍተኛ ሽኩቻ መቀስቀሱ ተነገረ።

ለባለፉት 13 ቀናት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ከብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ውጭ ማንም ያልተገኘበት ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን ደመቀ መኮንን እና አለምነው ከተሰብሳቢዎቹ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባታቸውም ተነግራል።

ደመቀ መኮንን ገዱ አንዳርጋቸውን ከአጥፊያችን ጋር በተለይም በአሜሪካ ከሚገኙ የአማራ ድርጅቶች ጋር እያበርክ ነው ሲል መድረክ ላይ መናገሩም ታውቃል።

የገዱ አንዳርጋቸው ደጋፊዎች በበኩላቸው የአማራ ህዝብ በብአዴን ደካማነት የተነሳ በሕወኃት ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመበት እንደሚገኝና ለዚህም ተጠያቂው የብአዴን ከፍተኛ አመራር በተለይም አለምነውና ደመቀ እንደሆኑ መናገራቸውን የተነገረ ሲሆን ወልቃይት የአማራ መሆኑን መንግሥት አምኖ ለተፈፀመው ግድያ ህዝቡን ሰብስቦ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ባፅንሆት መሟገታቸው ተገልፃል።


በሌላ በኩል ግምገማው ከመጀመሩ በፊት በባህርዳር ከተማ የአማራ ክልል ባለሐብቶችን ሰብስቦ ያነጋገረው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው ላይ በተገኙ ባለሐብቶች ከፍተኛ ሙገሳ ቀርቦለታል ተብላል። 

ነገር ግን ገዱ አንዳርጋቸው ከህወሀት ስርሀት ጋር ያገለገለ ያለ ህብረተሰቡ ሲበደል ሲገደልና ሲታሰር በቅርብ ሆኖ የሰራ ባለበት ሁኔታ ከገድዮቹ የህወሀት ባለስልጣናት ተለይቶ እንደማይታይ እንዲታወቅ ተብላል።   


በተያያዘ  ጎንደር ሁለት ከንቲባ የሚመራት ብቸኛዋ ከተማ ሆናለች። በጎንደር ህዝብ የተሻለ ተቀባይነት እንዳለው የሚነገረው የጎንደር ከንቲባ አቶ ተቀባ በህወሃቶች ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የተነሳ ሌላ ተጨማሪ ከንቲባ አቶ ከጎኑ እንደተመደበለት ለማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከሚያዝያ 21 እስከ 28 በጎንደር የተካሄደው የከተሞች ቀን ላይ የጎንደር ከንቲባ በመባል አቶ ተቀባ ተባባልና የቀድሞው የደህንነት ቢሮ ሠራተኛ አቶ አስቻለው ይመር ለታዳሚው መልእክት አስተላልፈው ታዳሚውን ግራ አጋብተዋል።