ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ተቃዋሚ ዮናታን ተስፋዬ ሽብርተኛ ተብሎ ሃያ ዓምታት ሊፈረደበት ነው

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ቢ ቢ ሲ ዛሬ ጠዋት እንደዘገበው ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ተቃዋሚን ዮናታን ተስፋዬን የኢትዮጵያ  መንግስት ሽብርተኛ ብሎ ሀያ ዓመታት ሊፈርድበት ነው።

መንግስት ዮናታን ተስፋዬን የከሰሰው በፌስ ቡክ ላይ ህዝብን የሚያነሳሳ “ሽብርተኛነትን” የሚያደፋፍር አስተያየት ሰጥተሃል በሚል ነው።

ዮናታን ተስፋዬ በፈረንጆች ዲሴምበር 2015 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል። 2015 ደግሞ በድፍን ኦሮሚያ ክልል ታላቅ የህዝብ ተቃውሞ ተነስቶ በነበረበት ወቅት ነበር።

የመንግስት ባለስልጣናት የከፋቸው ዮናታን ለተናገረው “ መንግስት ከሰላማዊ ውይይት ይልቅ የሀይል እርማጃ ወሰደ” ማለቱ ነው። አባባሉ እንደ ወንጀል ተወሰደበት ይላል የቢ ቢ ሲ ዝርዝር ዜና።

በኢትዮጵያ ገዢው መንግስትን በጸረ ሽብርተኛ ህጉ ዓለም ኮንኖታል ይላል ቢ ቢ ሲ።

ዮናታን ተስፋዬ ላይ የተመሰረተውን ክስ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል የሰባአዊ መብት ድርጅት “የሃሰት ክሶች” ብሎ በሜይ 2016 ተናግሮ ነበር

 በኢትዮጵያ ገዢው መንግስት የደነገገው “የጸረ ሽብርተኛ” አዋጅ መንግስትን ነክ የሆነ ማንኛውንም አስተያየት የሰጠን ሁሉ “ሽብርተኛ” የሚል ነው።

የዮናታን ተስፋዬን የክስ መስገብ ቢ ቢ ሲ እንዳስተረጎመው “ የምነግራችሁ የመንግስትን የጭቆና መንገዶች ሰባብሩ። አሁን ገዳዮቻችሁን ሽባ ማድረግ የምትችሉበት ጊዜ ነው” ብለሃል የሚል ነው።

መንግስት ዮናታን ተስፋዬ የመንግስት ተቃዋሚ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይ ነው። በዚህ 20 ዓመት እስራት ሊፈረድበት ነው ይላል ቢ ቢ ሲ አፍሪካ።

ቢ ቢ ስ በ2015 የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ተሰምቶ የማይታወቅ ታላቅ ተቃውሞ ገጥሞት አንደነበር  ጨምሯል። ተቃውሞውም ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍሎች መዛመቱን ተናግሯል። በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች 600 ሰዎችን መግደላቸው ከዛሬው ዜና ጋር አክሎ ተናግሯል። ይህ ደግሞ የራሱ የመንግስት ተቀጥላ የሆነው “ሰባዊ መብት ኮሚሽን” ያመነው መሆኑንም ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ኦክቶበር 2016 አንስቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳወጅም የተቃዋሚ መሪ ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና ይህኑ የመንግስት አዋጅ በመተቸታቸው ዛሬ በእስር እንደሚገኙም አክሎ አስረድቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለተቃዋሚ መሪዎች በጣም ረጅም ዓመታ የሚፍጁ ብይኖችን በመስጠት ለማስፈራራት መሞከሩ የተለመደ ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች።