የህወሃት ባለስላጣናት ህልም (በልዑል አለሜ)

0

መረጃ . . .

ግንቦት 09/2009

የህወሃት ከፍተኛ የተባሉና የተመረጡ ሚኒስቴሮች በሚኒስቴሮች ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ ቢሮ በሚወያዩበት ተመሳሳይ ወቅትና ሰዓት የህወሃት ወታደራዊ ጄኔራሎችንም በተመሳሳይ አጀንዳ በመከላከያ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ ቢሮ መቀመጣቸዉ ታወቀ።

በመሆኑም  በወ/ሪት አይሻ መሐመድ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በጌታሁን መኩሪያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በደምቢቱ ሃምቢሳ የህጻናትና የሴቶች ሚኒስቴር፣ በበቀለ ቡላዶ የንግድ ሚኒስቴር፣ በነገሪ ለንጮ የሐገር ዉስጥ ግንኙነት ሚኒስቴር እንዲሁም በከፍተኛ የሚኒስቴሮች ማእረግ ደረጃ በፈትለወርቅ ገብረ አግዚያብሐር ሰብሳቢነት የተካሄደዉ ምክክር ያለስምምነት ተጠናቋል።

በተለየ ሁኔታ የሐገሪቷን የባሕልና ቱሪዝም መድብል ታሪክ ከተበረዘና ዉጥንቅጡ ከወጣ ወዲህ ምን እንድናደርገዉ ትፈልጋላችሁ! በማለት የተሟገቱት ሚኒስቴር አይሻ ሞሃመድን ተከትሎ ሚኒስቴር ደምቢቱ ሃምቢሳም ህጻናትና ሴቶች፣፣፣፣ ሐገራዊ ታሪክና ባሕልን እንዲቀበሉ ለማድረግ ሌላ ትዉልድ ያስፈልገናል በማለት ተሳልቀዋል!

* ሐገሪቷን ለማዳን የመጨረሻ እርምጃ ያስፈልገናል *  በማለት የተጠራዉን ይህን ስብሰባ . . . . . . . . .. . . . . .ካፈረሳችሁት በኃላ እኛ ላይ ለመጫን የምትሞክሩት ጫናን እራሳችሁ ላይ ተሸከሙት…… እኛ ደግሞ የቻልነዉን እንሞክራለን ሲሉ ደምቢቱ ሐምቢሳ የህወሃት ነባር ሚኒስቴሮችን በቀጥታ ዘልፈዋል።

በተዘዋዋሪ መንገድ * ሐገሪቷን ለማዳን ምን እናድርግ በሚል * እርእሰ አጀንዳ የተሰባሰበዉ የህወሃት ወታደራዊ ወንጀለኛዉ ክንፍ በጄ/ አብረሃ አረጋዊ፣ አስራት ዶኖየሮ፣ ሃለፎም እጅጉ፣ ከዲር አራርሳ እና ጥጋቡ ይልማ እንዲሁም ሌሎችም የነበሩበት ሲሆን ሁሉም የተስማሙበት መሪ ሐሳብ ኤርትራ ዉስጥ የመሸጉትን የነጻነት ቀንዲሎች ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ማጥፋት ነዉ የሚል ድፍረት እንደሆነ ታዉቋል።

አጠቃላይ ሐገራችን ኢትዮጵያን እዚህ አስከፊ አደጋ ላይ የጣልዋት እነዚህ ባለስልጣናት ከመጥፋታቸዉ በፊት ከፍተኛ ጥፋት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚባልባቸዉን መንገዶች ሁሉ በመዝጋት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ታምኝ የዉስጥ ምንጫችን ጥሪ አስተላልፈዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

liul alem