አርበኞች ግንቦት7 በህወሃት ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

0
የአባይ ሚዲያ ዜና
መርጋ ደጀኔ

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ዛሬ ግንቦት 7 ለግንቦት 8-2009 ዓ.ም ለሊት 8፡55 ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ በጣራ ገዳም መሽጎ በነበረ የህወሃት መከላከያ ሠራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ።
 
የህወሃት መከላከያ ሠራዊት በተጠቀሰው ቦታ ላይ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።
 
የንቅናቄው ታጋዮች ወደ ወታደሮች ምሽግ ዘልቆ በመግባት 8 ወታደሮችን መግደላቸውንና አንድ ወታደር ማቁሰላቸውን፣ በድጋሜ 5፡00 ሰዓት ላይ በተደረገ ውጊያ ደግሞ 5 ገድለው 3 ማቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአርበኞቹ በኩል አንድ ታጋይ መቁሰሉንና የተሰዋ አባል እንደሌለ የድርጅቱ መግለጫ አመልክቷል።